ዘዳግም 32:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልዑል ለአሕዛብ ርስታቸውን በሰጠ ጊዜ፣ የሰውንም ዘር በለያየ ጊዜ፣ በእስራኤል ልጆች ቍጥር ልክ፣ የአሕዛብን ርስት ድንበር ለየ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልዑል ለአሕዛብ ርስታቸውን ባወረሰ ጊዜ፥ የሰውን ልጆች በለየ ጊዜ፥ እንደ እስራኤል ልጆች ቍጥር የአሕዛብን ድንበር አቆመ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልዑል እግዚአብሔር ለሕዝቡ ርስታቸውን ባከፋፈለ ጊዜ፥ የሰውን ዘር በለያየ ጊዜ፥ እንደ እስራኤል ልጆች ቊጥር ብዛት፥ ለሕዝቡ ድንበርን ሠራላቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልዑል አሕዛብን በከፈላቸው ጊዜ፥ የአዳምንም ልጆች በለያቸው ጊዜ፥ እንደ እግዚአብሔር መላእክት ቍጥር፥ አሕዛብን በየድንበራቸው አቆማቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ልዑል ለአሕዛብ ርስታቸውን ባወረሰ ጊዜ፥ 2 የአዳምን ልጆች በለየ ጊዜ፥ 2 እንደ እስራኤል ልጆች ቁጥር 2 የአሕዛብን ድንበር አቆመ። |
“ ‘ውሳኔው በመልእክተኞች ተገልጿል፤ ፍርዱም በቅዱሳኑ ተነግሯል፤ ይኸውም፣ ልዑል በሰዎች መንግሥታት ሁሉ ላይ እንደሚገዛና እነዚህንም መንግሥታት ለወደደው እንደሚሰጥ፣ ከሰዎችም የተናቁትን በላያቸው እንደሚሾም፣ ሕያዋን ሁሉ ያውቁ ዘንድ ነው።’
ከዐለታማ ተራሮች ጫፍ ሆኜ አየዋለሁ፤ በከፍታዎቹም ላይ ሆኜ እመለከተዋለሁ፤ ተለይቶ የሚኖረውን፣ ራሱንም ከሌሎች ሕዝቦች ጋራ የማይቈጥረውን ሕዝብ አያለሁ።
የዚያ የአምላክን ቃል የሚሰማ፣ ከልዑልም ዕውቀትን ያገኘው፣ ከሁሉን ቻይ ራእይ የሚገለጥለት፣ መሬት የተደፋው፣ ዐይኖቹም የተገለጡለት ሰው ንግር፤
ስለዚህ እስራኤል ብቻውን ያለ ሥጋት ይኖራል፤ የሰማያት ጠል በሚወርድበት፣ እህልና የወይን ጠጅ ባለበት ምድር፣ የያዕቆብን ምንጭ የሚነካው የለም።