ስለዚህ ምርኮኞቹ እንደ ተባለው አደረጉ፤ ካህኑ ዕዝራም ከእያንዳንዱ የቤተ ሰብ ምድብ አንዳንድ የቤተ ሰብ ኀላፊ የሆነ ሰው መረጠ፤ ሁሉም በየስማቸው ተመዘገቡ። ከዚያም በዐሥረኛው ወር በመጀመሪያው ቀን ጕዳዩን ለመመርመር ተቀመጡ፤
ዳንኤል 5:13 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳንኤልንም ወደ ንጉሡ አቀረቡት፤ ንጉሡም እንዲህ አለው፤ “ንጉሡ አባቴ ከይሁዳ ማርኮ ካመጣቸው መካከል አንዱ የሆንኸው ዳንኤል አንተ ነህን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያኑ ጊዜ ዳንኤል በንጉሡ ፊት ቀረበ፤ ንጉሡም እንዲህ አለው፦ “አባቴ ንጉሥ ናቡከደነፆር ማርኮ ካመጣቸው ከይሁዳ ስደተኞች መካከል አንዱ የሆንክ ዳንኤል አንተ ነህን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዚያን ጊዜም ዳንኤል ወደ ንጉሡ ፊት ገባ፥ ንጉሡም ተናገረው ዳንኤልም እንዲህ አለው፦ ንጉሡ አባቴ ከይሁዳ ከማረካቸው ከይሁዳ ምርኮኞች የሆንህ ዳንኤል አንተ ነህን? |
ስለዚህ ምርኮኞቹ እንደ ተባለው አደረጉ፤ ካህኑ ዕዝራም ከእያንዳንዱ የቤተ ሰብ ምድብ አንዳንድ የቤተ ሰብ ኀላፊ የሆነ ሰው መረጠ፤ ሁሉም በየስማቸው ተመዘገቡ። ከዚያም በዐሥረኛው ወር በመጀመሪያው ቀን ጕዳዩን ለመመርመር ተቀመጡ፤
ጌታም የይሁዳን ንጉሥ ኢዮአቄምን በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ካሉት ዕቃዎች ከጥቂቶቹ ጋራ በእጁ አሳልፎ ሰጠው፤ ወደ አምላኩ ቤት ወደ ባቢሎን ወሰዳቸው፤ በአምላኩም ግምጃ ቤት ውስጥ አኖራቸው።
አርዮክም ዳንኤልን ወዲያውኑ ወደ ንጉሡ በመውሰድ፣ “ሕልሙንና ትርጕሙን ለንጉሡ መግለጥ የሚችል ሰው ከይሁዳ ምርኮኞች መካከል አግኝቻለሁ” አለው።
ንጉሡም ዳንኤልን በከፍተኛ ሥልጣን ላይ አስቀመጠው፤ እጅግ ብዙ ስጦታዎችንም ሰጠው፤ የመላው ባቢሎን አውራጃ ገዥ አደረገው፤ በባቢሎን ጠቢባን ሁሉ ላይም አለቃ አድርጎ ሾመው።
በመንግሥትህ ውስጥ የቅዱሳን አማልክት መንፈስ ያለበት አንድ ሰው አለ፤ ይህ ሰው በአባትህ ዘመን እንደ አማልክት ጥበብና ማስተዋል፣ ዕውቀትም የሞላበት ሆኖ ተገኝቷል፤ አባትህ ንጉሥ ናቡከደነፆርም የጠንቋዮች፣ የአስማተኞች፣ የኮከብ ቈጣሪዎችና የመተተኞች አለቃ አደረገው።
ቤልሻዛር የወይን ጠጁን እየጠጣ ሳለ፣ አባቱ ናቡከደነፆር ከኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ ያመጣቸውን የወርቅና የብር መጠጫዎችን እርሱና መኳንንቱ፣ ሚስቶቹና ቍባቶቹ ይጠጡባቸው ዘንድ እንዲያመጡለት አዘዘ።
እነርሱም ንጉሡን፣ “ንጉሥ ሆይ፤ ከይሁዳ ምርኮኞች አንዱ የሆነው ዳንኤል፣ አንተንም ሆነ በጽሑፍ ያወጣኸውን ዐዋጅ አያከብርም፤ አሁንም በቀን ሦስት ጊዜ ወደ አምላኩ ይጸልያል” አሉት።
እኔ ዳንኤል ዐቅሜ ተሟጥጦ ነበር፤ ለብዙ ቀናት ታመምሁ፤ ተኛሁም። ከዚያም በኋላ ተነሥቼ ወደ ንጉሡ ሥራ ሄድሁ። ባየሁት ራእይ ተደናግጬ ነበር፤ ነገሩም አልገባኝም።