ዳንኤል 11:38 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእነርሱም ምትክ የምሽጎችን አምላክ ያከብራል፤ አባቶች የማያውቁትን አምላክ በወርቅ፣ በብር፣ በከበሩ ድንጋዮችና በውድ ስጦታዎች ያከብራል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከነዚህ ይልቅ፥ ምሽጎችን የሚጠብቅ ባዕድ አምላክን ያከብራል፤ በቀድሞ አባቶቹ ላልታወቀ አምላክ ወርቅ፥ ብር፥ ጌጣጌጥ የከበሩ ድንጋዮችንና ሌሎችንም ውድ ስጦታዎች በማቅረብ ያከብራል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእነዚህ ፋንታ ግን የአምባዎቹን አምላክ ያከብራል፥ አባቶቹም ያላወቁትን አምላክ በወርቅና በብር በዕንቍና በከበረ ነገር ያከብረዋል። |
ሴቶች ለሚወድዱትም ሆነ ለአባቶቹ አማልክት ክብርን አይሰጥም፤ ማንኛውንም አምላክ አያከብርም፤ ነገር ግን ራሱን ከእነዚህ ሁሉ በላይ ከፍ ከፍ ያደርጋል።
በባዕድ አምላክ ርዳታ ጽኑ ምሽጎችን ይወጋል፤ ለርሱ የሚገዙትን በእጅጉ ያከብራቸዋል፤ በብዙ ሕዝብ ላይ ገዦች ያደርጋቸዋል፤ ምድሩንም በዋጋ ያከፋፍላቸዋል።
“ከዘመዶቿ አንዱ ስፍራዋን ሊይዝ ይነሣል፤ የሰሜንን ንጉሥ ሰራዊት ይወጋል፤ ምሽጎቹንም ጥሶ ይገባል፤ ከእነርሱም ጋራ ተዋግቶ ድል ያደርጋል።
ጭነቱም፦ ወርቅ፣ ብር፣ የከበረ ድንጋይ፣ ዕንቍ፣ ከተልባ እግር የተሠራ ቀጭን ልብስ፣ ሐምራዊ ልብስ፣ ሐር ልብስ፣ ቀይ ልብስ፣ መልካም ሽታ ያለው ዕንጨት ሁሉ፣ ከዝሆን ጥርስ፣ ከውድ ዕንጨት፣ ከናስ፣ ከብረትና ከእብነ በረድ የተሠራ ዕቃ ሁሉ፣