“እንዲህ አይደለም ጌታዬ፤ ስማኝ፤ ዕርሻውን በውስጡ ካለው ዋሻ ጋራ ውሰደው። እነሆ፤ በወገኖቼ ኬጢያውያን ፊት ሰጥቼሃለሁ፤ ሬሳህን ቅበርበት።”
2 ሳሙኤል 24:24 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሡ ግን ኦርናን፣ “እንዲህ አይደረግም፤ ዋጋውን ላንተ መክፈል አለብኝ፤ ለአምላኬም ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ያለ ዋጋ አላቀርብም” አለው። ስለዚህም ዳዊት ዐውድማውንና በሬዎቹን በዐምሳ ሰቅል ብር ገዛ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሡ ግን ኦርናን፥ “መክፈል ያለብኝን ዋጋ ላንተ ከፍዬ እንጂ እንዲሁማ አይሆንም፤ ለጌታም ለአምላኬ የሚቃጠል መሥዋዕት ያለ ዋጋ አላቀርብም” አለው። ስለዚህም ዳዊት ዐውድማውንና በሬዎቹን በአምሳ ሰቅል ብር ገዛ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሥ ዳዊት ግን “ይህስ አይሆንም፤ ዋጋውን መክፈል አለብኝ፤ እኔ ምንም ዋጋ ያላወጣሁበትን ነገር ለአምላኬ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አድርጌ ማቅረብ አይገባኝም” አለው፤ ከዚህም በኋላ ዳዊት አውድማውንና በሬዎቹን በኀምሳ ጥሬ ብር ገዛ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡም ኦርናን፥ “እንዲህ አይደለም፤ ነገር ግን በዋጋ ከአንተ እገዛለሁ፤ ለአምላኬም ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ያለ ዋጋ አላቀርብም” አለው። ዳዊትም አውድማውንና በሬዎቹን በአምሳ ሰቅል ብር ገዛ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም ኦርናን፦ እንዲህ አይደለም፥ ነገር ግን በዋጋ ከአንተ እገዛለሁ፥ ለአምላኬም ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ያለዋጋ አላቀርብም አለው። ዳዊትም አውድማውንና በሬዎቹን በአምሳ ሰቅል ብር ገዛ። |
“እንዲህ አይደለም ጌታዬ፤ ስማኝ፤ ዕርሻውን በውስጡ ካለው ዋሻ ጋራ ውሰደው። እነሆ፤ በወገኖቼ ኬጢያውያን ፊት ሰጥቼሃለሁ፤ ሬሳህን ቅበርበት።”
ከዚያም ዳዊት፣ “ከእንግዲህ የእግዚአብሔር አምላክ ቤት በዚህ ይሆናል፤ እንዲሁም ስለ እስራኤል የሚቃጠል መሥዋዕት የሚቀርብበት መሠዊያ በዚሁ ይቆማል” አለ።