እነርሱም በዮርዳኖስ ማዶ ካለው አጣድ ከተባለው ዐውድማ ሲደርሱ፣ ድምፃቸውን ከፍ በማድረግ ምርር ብለው አለቀሱ፤ ዮሴፍም በዚያ ለአባቱ ሰባት ቀን ልቅሶ ተቀመጠ።
2 ሳሙኤል 24:18 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ቀን ጋድ ወደ ዳዊት ዘንድ ሄዶ፣ “ውጣና በኢያቡሳዊው በኦርና ዐውድማ ላይ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሥራ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያን ቀን ጋድ ወደ ዳዊት መጥቶ፥ “ውጣና በኢያቡሳዊው በኦርና ዐውድማ ላይ ለጌታ መሠዊያ ሥራ” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያው ዕለት ነቢዩ ጋድ ወደ ዳዊት ሄዶ “ወደ ኦርና አውድማ ሄደህ ለእግዚአብሔር መሠዊያውን ሥራ!” አለው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ቀን ጋድ ወደ ዳዊት መጥቶ፥ “ውጣ፤ በኢያቡሳዊው በኦርና አውድማ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሥራ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ቀን ጋድ ወደ ዳዊት መጥቶ፦ ውጣ፥ በኢያቡሳዊው በኦርና አውድማ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሥራ አለው። |
እነርሱም በዮርዳኖስ ማዶ ካለው አጣድ ከተባለው ዐውድማ ሲደርሱ፣ ድምፃቸውን ከፍ በማድረግ ምርር ብለው አለቀሱ፤ ዮሴፍም በዚያ ለአባቱ ሰባት ቀን ልቅሶ ተቀመጠ።
ሰሎሞንም በኢየሩሳሌም እግዚአብሔር ለአባቱ ለዳዊት በተገለጠበት በሞሪያ ተራራ ላይ በኢያቡሳዊው በኦርና ዐውድማ ዳዊት ባዘጋጀው ቦታ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ መሥራት ጀመረ።
ደሙን ከአፋቸው፣ አስጸያፊውንም ምግብ ከመንጋጋቸው አወጣለሁ። የተረፉት ለአምላካችን ይሆናሉ፤ በይሁዳም አለቆች ይሆናሉ፤ አቃሮንም እንደ ኢያቡሳዊ ይሆናል።