ከራፋይም ዘሮች አንዱ የሆነ ይሽቢብኖብ የተባለ፣ የናስ ጦሩ ሦስት መቶ ሰቅል የሚመዝንና አዲስ ሰይፍ የታጠቀ ሰው ነበረ፤ እርሱም ዳዊትን ለመግደል ዐሰበ።
2 ሳሙኤል 21:18 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ በኋላ ጎብ በተባለ ስፍራ ከፍልስጥኤማውያን ጋራ ሌላ ጦርነት ተደረገ። በዚያ ጊዜም ኩሳታዊው ሴቦካይ፣ ከራፋይም ዘሮች አንዱ የሆነውን፣ ሳፍን ገደለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህ በኋላ ጎብ በተባለ ስፍራ ከፍልስጥኤማውያን ጋር ሌላ ጦርነት ተደረገ። በዚያን ጊዜም የሑሻው ተወላጅ ሲበካይ፥ ከራፋይም ዘሮች አንዱ የሆነውን ሳፍን ገደለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ጎብ ተብሎ በሚጠራ ስፍራ ከፍልስጥኤማውያን ጋር ጦርነት ተደረገ፤ በዚህን ጊዜ የሑሻ ተወላጅ የሆነው ሲበካይ፥ ሳፍ ተብሎ የሚጠራውን ከራፋይም ወገን የነበረውን ኀያል ሰው ገደለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚህም በኋላ እንደ ገና በጎብ ላይ ከፍልስጥኤማውያን ጋር ጦርነት ሆነ፤ ያን ጊዜም አስጣጦታዊው ሴቤኮይ ከራፋይም ወገን የሆነውን ሳፍን ገደለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚህም በኋላ እንደ ገና በጎብ ላይ ከፍልስጥኤማውያን ጋር ሰልፍ ሆነ፥ ኩሳታዊውም ሴቦካይ ከራፋይም ወገን የነበረውን ሳፍን ገደለ። |
ከራፋይም ዘሮች አንዱ የሆነ ይሽቢብኖብ የተባለ፣ የናስ ጦሩ ሦስት መቶ ሰቅል የሚመዝንና አዲስ ሰይፍ የታጠቀ ሰው ነበረ፤ እርሱም ዳዊትን ለመግደል ዐሰበ።
እንደ ገና ጋት ላይ በተደረገው ጦርነት በእያንዳንዱ እጁና በእያንዳንዱ እግሩ ስድስት ስድስት ጣቶች በአጠቃላይ ሃያ አራት ጣቶች የነበሩት አንድ ግዙፍ ሰው ነበረ፤ እርሱም ደግሞ ከራፋይም ዘር ነበረ።