2 ሳሙኤል 14:20 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም አገልጋይህ ኢዮአብ ይህን ያደረገውም ያለውን ሁኔታ ለመለወጥ ሲል ነው፤ ነገር ግን ጌታዬ የእግዚአብሔርን መልአክ ጥበብ የመሰለ ጥበብ ስላለው፣ በምድሪቱ ላይ የሚሆነውን ነገር ሁሉ ያውቃል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አገልጋይህ ኢዮአብ ይህን ያደረገውም የነገሩን መልክ ለመለወጥ ሲል ነው፤ ነገር ግን ጌታዬ ያለው ጥበብ የእግዚአብሔርን መልአክ ጥበብ ስለሚመስል፥ በምድሪቱ ላይ የሚሆነውን ነገር ሁሉ ያውቃል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱም ይህን ያደረገው ነገሮችን ሁሉ ለማስተካከል በማሰብ ነው፤ ንጉሥ ሆይ! አንተ ግን እንደ እግዚአብሔር መልአክ ጥበበኛ ነህ፤ የሚሆነውንም ነገር ሁሉ ታውቃለህ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህን ነገር እናገር ዘንድ እንድመጣ ይህን ምክር ያደረገ አገልጋይህ ኢዮአብ ነው። ጌታዬ ግን በዚህ ዓለም የሚደረገውን ሁሉ ታውቅ ዘንድ እንደ መልአከ እግዚአብሔር ጥበብ ጥበበኛ ነህ፤” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባሪያህ ኢዮአብ የዚህ ነገር መልክ እንዲለውጥ አደረገ፥ ነገር ግን የእግዚአብሔር መልአክ ጠቢብ እንደ ሆነ፥ አንተም ጌታዬ በምድር ላይ ያለውን ነገር ሁሉ ታውቅ ዘንድ ጠቢብ ነህ አለች። |
“አሁንም አገልጋይህ፤ ‘ንጉሥ ጌታዬ በጎውንና ክፉውን በመለየት እንደ እግዚአብሔር መልአክ ስለ ሆነ፣ የጌታዬ የንጉሡ ቃል ያጽናናኝ፤ እግዚአብሔር አምላክህም ካንተው ጋራ ይሁን’ ትላለች።”
በሌላ በኩል ደግሞ በነፍሴ ቈርጬ ሕይወቱን ባጠፋው ኖሮ፣ ከንጉሡ ተደብቆ የሚቀር ነገር ስለሌለ፣ አንተም ራስህ አትቀርበኝም ነበር” ብሎ መለሰለት።
በጌታዬ በንጉሡ ፊትም የእኔን የባሪያህን ስም አጥፍቷል፤ መቼም ንጉሥ ጌታዬ እንደ እግዚአብሔር መልአክ ስለ ሆንህ ደስ ያለህን ሁሉ አድርግ።
የአባቴ ቤት ሁሉ ከንጉሥ ጌታዬ ሞት እንጂ ሌላ የሚገባው አልነበረም፤ አንተ ግን ባሪያህን በማእድህ ከሚካፈሉት ጋራ አስቀመጥኸው፤ ከዚህ በላይ ይደረግልኝ ብዬ ንጉሡን ለመጠየቅ ምን መብት አለኝ?”
ስለዚህም ዳዊት እግዚአብሔርን ጠየቀ፤ እግዚአብሔርም እንዲህ አለው፤ “በስተ ኋላቸው በኩል በመክበብ በሾላው ዛፍ ፊት ለፊት ግጠማቸው እንጂ በቀጥታ ወዳሉበት አትውጣ፤
አንኩስም እንዲህ አለው፤ “በእኔ ዘንድ እንደ እግዚአብሔር መልአክ መልካም እንደ ሆንህ ዐውቃለሁ፤ የፍልስጥኤማውያን አዛዦች ግን፣ ‘ዐብሮን ለጦርነት መውጣት የለበትም’ ብለዋል።