2 ነገሥት 22:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰዎቹ ታማኞች ስለ ሆኑም የተሰጣቸውን ገንዘብ መቈጣጠር አያስፈልግም።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሥራው ኃላፊዎች ፍጹም ታማኞች ስለ ሆኑ እነርሱን ስለ ገንዘቡ አወጣጥ መቆጣጠር አያስፈልግም።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሥራው ኀላፊዎች ፍጹም ታማኞች ስለ ሆኑ እነርሱን ስለ ገንዘቡ አወጣጥ መቈጣጠር አያስፈልግም።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን እነርሱ በእምነት ይሠሩ ነበርና የሰጡአቸውን ገንዘብ አይቈጣጠሩአቸውም ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን እነርሱ የታመኑ ስለሆኑ በእጃቸው ስለ ተሰጠው ገንዘብ አይቈጣጠሩአቸው።” |
የሚከፍሉትም ለየእጅ ጥበብ ባለሙያዎች፣ ለግንበኞችና ለድንጋይ ጠራቢዎች ነው። እንዲሁም ለቤተ መቅደሱ ዕድሳት ሥራ የሚሆኑ ዕንጨቶችና ጥርብ ድንጋዮች ይግዙበት።
ከጨረሱም በኋላ ቀሪውን ገንዘብ ወደ ንጉሡና ወደ ዮዳሄ አመጡ፤ በገንዘቡም የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ዕቃዎች ማለትም ለአገልግሎትና ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚውሉ ዕቃዎች እንደዚሁም ጭልፋዎችና ሌሎች የወርቅና የብር ዕቃዎችም ተሠሩ። ዮዳሄ በሕይወት በነበረበት ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የሚቃጠል መሥዋዕት ዘወትር ይቀርብ ነበር።
በኢየሩሳሌምም ላይ ወንድሜን አናኒን እንዲሁም ፍጹም ታማኝና ከሌሎች ሰዎች ይልቅ እግዚአብሔርን ይበልጥ የሚፈራውን የግንቡን አዛዥ ሐናንያን ኀላፊ አደረግኋቸው።