ስለዚህ ኤልያስ ከዚያ ተነሥቶ ሲሄድ፣ የሣፋጥን ልጅ ኤልሳዕን ዐሥራ ሁለት ጥማድ በሬ አውጥቶ ራሱ በዐሥራ ሁለተኛው ጥማድ በሬ ሲያርስ አገኘው። ኤልያስም ወደ እርሱ መጥቶ መጐናጸፊያውን በላዩ ጣለበት።
2 ነገሥት 2:13 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም ከኤልያስ የወደቀውን ካባ አነሣ፤ ተመልሶም በዮርዳኖስ ወንዝ ዳር ቆመ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከኤልያስም የወደቀውን ካባ ከመሬት አነሣ፤ ከዚያም ሄዶ በዮርዳኖስ ወንዝ ዳርቻ ቆመ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከኤልያስም የወደቀውን ካባ ከመሬት አነሣ፤ ከዚያም ሄዶ በዮርዳኖስ ወንዝ ዳርቻ ቆመ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኤልያስም መጠምጠሚያውን ለኤልሳዕ ጣለለት፤ በኤልሳዕም ራስ ላይ ዐረፈ። ኤልሳዕም ተመልሶ በዮርዳኖስ ዳር ቆመ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከኤልያስም የወደቀውን መጎናጸፊያ አነሣ፤ ተመልሶም በዮርዳኖስ ዳር ቆመ። |
ስለዚህ ኤልያስ ከዚያ ተነሥቶ ሲሄድ፣ የሣፋጥን ልጅ ኤልሳዕን ዐሥራ ሁለት ጥማድ በሬ አውጥቶ ራሱ በዐሥራ ሁለተኛው ጥማድ በሬ ሲያርስ አገኘው። ኤልያስም ወደ እርሱ መጥቶ መጐናጸፊያውን በላዩ ጣለበት።
ኤልሳዕም ይህን አይቶ፣ “አባቴ አባቴ የእስራኤል ሠረገሎችና ፈረሰኞች!” ብሎ ጮኸ፤ ዳግመኛም ኤልያስን አላየውም፤ ከዚያም የገዛ ልብሱን ይዞ ከሁለት ቦታ ቀደደው።
ከኤልያስ፣ የወደቀውንም ካባ ይዞ ውሃውን መታና፣ “የኤልያስ አምላክ እግዚአብሔር ወዴት ነው?” አለ። ውሃውን ሲመታውም ውሃው በግራና በቀኝ ተከፈለ፤ ኤልሳዕም ተሻገረ።
በድንጋይ ተወገሩ፤ በመጋዝ ለሁለት ተሰነጠቁ፤ በሰይፍ ተወግተው ሞቱ፤ እየተጐሳቈሉ፣ እየተሰደዱና እየተንገላቱ የበግና የፍየል ቈዳ ለብሰው ዞሩ፤
እርሱም፣ “ምን ይመስላል?” ሲል ጠየቃት። እርሷም፣ “ካባ የለበሰ አንድ ሽማግሌ ሰው እየወጣ ነው” አለችው። ሳኦልም ሴትዮዋ ያየችው ሳሙኤል መሆኑን ዐወቀ፤ በመሬትም ላይ ተደፍቶ እጅ ነሣ።