በዚህ ጊዜ ኤልሳዕ ለሞት ባደረሰው ሕመም ታምሞ ነበር። የእስራኤልም ንጉሥ ዮአስ ሊጠይቀው ወርዶ አለቀሰለት፤ “ወየው አባቴን! ወየው አባቴን! ወየው የእስራኤል ሠረገሎችና ፈረሰኞች!” እያለም ጮኸ።
2 ነገሥት 13:15 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኤልሳዕም፣ “አንድ ቀስትና ፍላጾች አምጣ” አለው፤ እርሱም አመጣ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኤልሳዕም ንጉሡን “አንድ ቀስትና ፍላጻዎች ውሰድ” ሲል አዘዘው፤ ዮአስም እንደ ታዘዘው አደረገ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኤልሳዕም ንጉሡን “አንድ ቀስትና ፍላጻዎች ውሰድ” ሲል አዘዘው፤ ዮአስም እንደታዘዘው አደረገ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኤልሳዕም፥ “ቀስትህንና ፍላጻዎችህን ውሰድ” አለው፤ ቀስቱንና ፍላጻዎቹንም ወሰደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኤልሳዕም “ቀስትና ፍላጻዎች ውሰድ፤” አለው፤ ቀስቱንና ፍላጻዎችንም ወሰደ። |
በዚህ ጊዜ ኤልሳዕ ለሞት ባደረሰው ሕመም ታምሞ ነበር። የእስራኤልም ንጉሥ ዮአስ ሊጠይቀው ወርዶ አለቀሰለት፤ “ወየው አባቴን! ወየው አባቴን! ወየው የእስራኤል ሠረገሎችና ፈረሰኞች!” እያለም ጮኸ።
ወደ እኛም መጣና የጳውሎስን መታጠቂያ ወሰደ፤ የራሱንም እጅና እግር በማሰር፣ “መንፈስ ቅዱስ፣ ‘በኢየሩሳሌም ያሉ አይሁድ የዚህን መታጠቂያ ባለቤት እንዲህ አድርገው በማሰር ለአሕዛብ አሳልፈው ይሰጡታል’ ይላል” አለ።