ጻድቅ ሰው ይቅጣኝ፤ ይህ በጎነት ነው፤ ይገሥጸኝም፤ በራሴ ላይ እንደሚፈስስ ዘይት ነው፤ ራሴም ይህን እንቢ አይልም። ጸሎቴ ግን በክፉዎች ተግባር ላይ ነው።
2 ቆሮንቶስ 7:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የተጽናናነውም በመምጣቱ ብቻ ሳይሆን፣ እርሱንም ልታጽናኑት በመቻላችሁ ጭምር ነው። ስለ ናፍቆታችሁ፣ ስለ ሐዘናችሁና ለእኔም ስላላችሁ ቅናት ነግሮናል፤ ስለዚህ ከመቼውም ጊዜ ይልቅ ደስ ብሎኛል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመምጣቱም ብቻ አይደለም፤ ነገር ግን ናፍቆታችሁንና ልቅሶአችሁን ስለ እኔም የነበራችሁን ቅንዓት ሲነገረን በእናንተ ስለተጽናናን ማለቴ ነው፤ ስለዚህም ከመቼውም ጊዜ ይልቅ ደስ አለኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የተጽናናነውም በእርሱ መምጣት ብቻ ሳይሆን እናንተ እርሱን ያጽናናችሁት መሆኑን በመስማታችንም ጭምር ነው፤ ስለ እኔ ያላችሁን ናፍቆትና ሐዘን ጭንቀትም በነገረን ጊዜ ይበልጥ ደስ አለኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመምጣቱ ብቻ አይደለም፤ በአጽናናችሁት ማጽናናትም ነው እንጂ፤ ለእኛ እንደምታስቡና እንደምትቀኑ ፍቅራችሁን ነግሮናል፤ ይህንም ሰምቼ ደስታዬ በእናንተ በዛ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመምጣቱም ብቻ አይደለም ነገር ግን ናፍቆታችሁንና ልቅሶአችሁን ስለ እኔም ቅንዓታችሁን ሲናገረን በእናንተ ላይ በተጽናናበት መጽናናት ደግሞ ነው፤ ስለዚህም ከፊት ይልቅ ደስ አለን። |
ጻድቅ ሰው ይቅጣኝ፤ ይህ በጎነት ነው፤ ይገሥጸኝም፤ በራሴ ላይ እንደሚፈስስ ዘይት ነው፤ ራሴም ይህን እንቢ አይልም። ጸሎቴ ግን በክፉዎች ተግባር ላይ ነው።
በዚህ ጊዜ ጴጥሮስ፣ “ዶሮ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ” ብሎ ኢየሱስ የተናገረው ቃል ትዝ አለው፤ ጴጥሮስም ወደ ውጭ ወጥቶ ምርር ብሎ አለቀሰ።
በምንም ዐይነት መንገድ ዐፍሬ እንዳልገኝ ጽኑ ናፍቆትና ተስፋ አለ፤ ነገር ግን እንደ ወትሮው ሁሉ ዛሬም በሕይወትም ሆነ በሞት ክርስቶስ በሥጋዬ እንዲከበር ሙሉ ድፍረት ይኖረኛል።
ምንም በሥጋ ከእናንተ ርቄ ብገኝ በመንፈስ ከእናንተ ጋራ ነኝና በሥርዐት መኖራችሁንና በክርስቶስ ያላችሁን ጽኑ እምነት እያየሁ ደስ ይለኛል።
አሁን ግን ጢሞቴዎስ ከእናንተ ዘንድ ወደ እኛ መጥቶ ስለ እምነታችሁና ስለ ፍቅራችሁ መልካም ዜና አሰምቶናል። ደግሞም እኛን ሁልጊዜ በመልካም እንደምታስታውሱንና እኛ እናንተን ለማየት የምንናፍቃችሁን ያህል እናንተም እኛን ለማየት እንደምትናፍቁ ነግሮናል።
ወዳጆች ሆይ፤ ዐብረን ስለምንካፈለው ድነት ልጽፍላችሁ እጅግ ጓጕቼ ነበር፤ ነገር ግን ለቅዱሳን አንዴና ለመጨረሻ ስለ ተሰጠው እምነት እንድትጋደሉ ለመምከር እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ።