1 ሳሙኤል 26:25 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ሳኦል ዳዊትን፣ “ልጄ ዳዊት ሆይ፤ የተባረክህ ሁን፤ ታላቅ ነገር ታደርጋለህ፤ በርግጥም ይከናወንልሃል” አለው። ስለዚህም ዳዊት ወደሚሄድበት ሄደ፤ ሳኦልም ወደ ቤቱ ተመለሰ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ሳኦል ዳዊትን፥ “ልጄ ዳዊት ሆይ፤ የተባረክህ ሁን፤ ብዙ ነገር ታደርጋለህ፤ በእርግጥም ይከናወንልሃል” አለው። ስለዚህም ዳዊት ወደሚሄድበት ሄደ፤ ሳኦልም ወደ ስፍራው ተመለሰ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳኦልም ዳዊትን “ልጄ ሆይ፥ እግዚአብሔር ይባርክህ! ብዙ ነገርን ታደርጋለህ፤ ይሳካልሃልም” አለው። ስለዚህም ዳዊት ወደ ፈለገበት ቦታ ሄደ፤ ሳኦልም ወደ ቤቱ ተመለሰ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳኦልም ዳዊትን፥ “ልጄ ዳዊት ሆይ! ቡሩክ ሁን፤ ማድረግን ታደርጋለህ፤ መቻልንም ትችላለህ” አለው። ዳዊትም መንገዱን ሄደ፤ ሳኦልም ወደ ስፍራው ተመለሰ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳኦል ዳዊትን፦ ልጄ ዳዊት ሆይ፥ ቡሩክ ሁን፥ ማድረግን ታደርጋለህ፥ መቻልንም ትችላለህ አለው። ዳዊትም መንገዱን ሄደ፥ ሳኦልም ወደ ሰፍራው ተመለሰ። |
በአንቺ ላይ እንዲደገን የተበጀ መሣሪያ ይከሽፋል፤ የሚከስሽንም አንደበት ሁሉ ትረቺያለሽ፤ እንግዲህ የእግዚአብሔር ባሪያዎች ርስት ይህ ነው፤ ከእኔ የሚያገኙትም ጽድቃቸው ይኸው ነው፤” ይላል እግዚአብሔር።