1 ሳሙኤል 23:10 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ዳዊት እንዲህ አለ፤ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ ሳኦል ወደ ቅዒላ መጥቶ፣ በእኔ ምክንያት ከተማዪቱን ለማጥፋት ማሰቡን ባሪያህ በትክክል ሰምቷል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ዳዊት እንዲህ አለ፤ “የእስራኤል አምላክ ጌታ ሆይ፤ ሳኦል ወደ ቅዒላ መጥቶ፥ በእኔ ምክንያት ከተማዪቱን ለማጥፋት ማሰቡን ባርያህ በትክክል ሰምቷል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በኋላ ዳዊት እንዲህ አለ፤ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! በአገልጋይህ በእኔ ሰበብ ሳኦል መጥቶ ቀዒላን ለመደምሰስ ማቀዱን ሰምቻለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም፥ “የእስራኤል አምላክ አቤቱ! በእኔ ምክንያት ከተማዪቱን ያጠፋ ዘንድ ሳኦል ወደ ቂአላ ሊመጣ እንደሚፈልግ እኔ ባሪያህ ፈጽሜ ሰምቻለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም፦ የእስራኤል አምላክ አቤቱ፥ በእኔ ምክንያት ከተማይቱን ያጠፋ ዘንድ ሳኦል ወደ ቅዒላ ሊመጣ እንደሚፈልግ እኔ ባሪያህ ፈጽሜ ሰምቻለሁ። |
ይልቁንም መርዶክዮስ ከእነማን ወገን መሆኑን በተረዳ ጊዜ፣ መርዶክዮስን ብቻ መግደል እንደ ኢምንት ቈጠረው፤ ስለዚህ ሐማ በመላው የጠረክሲስ መንግሥት ውስጥ የሚገኙትንና የመርዶክዮስ ወገን የሆኑትን አይሁድ ሁሉ ለማጥፋት ዘዴ ፈለገ።
የካህናቱንም ከተማ ኖብን በሰይፍ መታት፣ በዚያ የሚኖሩትንም ወንዶችንና ሴቶችን፣ ልጆችንና ጡት የሚጠቡ ሕፃናትን፣ እንዲሁም በሬዎችንና አህያዎችን፣ በጎችንም ሁሉ በሰይፍ ስለት ፈጃቸው።
የቅዒላ ገዦች አሳልፈው ይሰጡኝ ይሆን? ባሪያህ እንደሰማውም ሳኦል ወደዚህ ይወርድ ይሆን? የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ ለባሪያህ እንድትነግረው እለምንሃለሁ።” እግዚአብሔርም፣ “አዎን ይወርዳል” አለው።