1 ሳሙኤል 2:31 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነሆ፤ በዘርህ ሽማግሌ እንዳይገኝ ያንተን ኀይልና የአባትህን ቤተ ሰብ ኀይል የምሰብርበት ጊዜ ይመጣል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆ፥ ለቤትህ ሽማግሌ እንዳይገኝ፥ የአንተንም ክንድ፥ የአባትህንም ቤት ክንድ የምሰብርበት ዘመን ይመጣል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነሆ፥ ከአንተ ቤተሰብ መካከል አንድም ሰው ወደ ሽምግልና ዕድሜ እንዳይደርስ አንተንና የአባቶችህን ቤተሰብ የማጠፋበት ጊዜ እየተቃረበ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ፥ ዘርህንም፥ የአባትህንም ቤት ዘር የማጠፋበት ዘመን ይመጣል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆ፥ ለቤትህ ሽማግሌ እንዳይገኝ፥ ክንድህን የአባትህንም ቤት ክንድ የምሰብርበት ዘመን ይመጣል። |
ኤፉድ ይለብስ የነበረውም አኪያ በመካከላቸው ነበር። እርሱም በሴሎ የእግዚአብሔር ካህን የነበረው የዔሊ ልጅ፣ የፊንሐስ ልጅ የኢካቦድ ወንድም የአኪጦብ ልጅ ነበር። ዮናታን አለመኖሩን ግን ያወቀ ሰው አልነበረም።
ፍልስጥኤማውያን እስራኤልን ለመግጠም ሰራዊታቸውን አሰለፉ፤ ጦርነቱ እንደ ተፋፋመም፣ እስራኤላውያን በፍልስጥኤማውያን ተሸነፉ፤ በጦርነቱም ላይ አራት ሺሕ ያህል እስራኤላውያን ተገደሉ።