የገበሩትም መንግሥታት ኤዶምና ሞዓብ፣ አሞናውያን፣ ፍልስጥኤማውያንና አማሌቃውያን ነበሩ። እንዲሁም ከሱባ ንጉሥ ከረአብ ልጅ ከአድርአዛር የወሰደውን ምርኮ ለእግዚአብሔር ቀደሰ።
1 ሳሙኤል 15:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የአማሌቃውያንን ንጉሥ አጋግን ከነሕይወቱ ማረከው፤ ሕዝቡን ሁሉ በሰይፍ ስለት ፈጽሞ አጠፋቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአማሌቃውያንን ንጉሥ አጋግን ከነሕይወቱ ማረከው፤ ሕዝቡን ሁሉ በሰይፍ ስለት ፈጽሞ አጠፋቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዐማሌቅ ንጉሥ የነበረውን አጋግን በሕይወት ማርኮ፥ ሕዝቡን ሁሉ በሰይፍ ፈጀ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአማሌቅንም ንጉሥ አጋግን በሕይወቱ ማረከው፤ የኢያሬምንም ሕዝብ ሁሉ በሰይፍ ስለት ፈጽሞ አጠፋቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአማሌቅንም ንጉሥ አጋግን በሕይወቱ ማረከው፥ ሕዝቡንም ሁሉ በሰይፍ ስለት ፈጽሞ አጠፋቸው። |
የገበሩትም መንግሥታት ኤዶምና ሞዓብ፣ አሞናውያን፣ ፍልስጥኤማውያንና አማሌቃውያን ነበሩ። እንዲሁም ከሱባ ንጉሥ ከረአብ ልጅ ከአድርአዛር የወሰደውን ምርኮ ለእግዚአብሔር ቀደሰ።
የቀሩት ወደ አፌቅ ከተማ ሸሹ፤ በዚያም በሃያ ሰባቱ ሺሕ ላይ ቅጥሩ ተንዶ ወደቀባቸው። ቤን ሃዳድም ወደ ከተማዪቱ ሸሽቶ በመሄድ ወደ አንዲት እልፍኝ ገብቶ ተደበቀ።
ከዚህም ነገር በኋላ ንጉሥ ጠረክሲስ የአጋጋዊውን የሐመዳቱን ልጅ ሐማን ከፍ ከፍ አደረገው፤ ከሌሎቹም መኳንንት ሁሉ ከፍተኛውን ሥልጣን በመስጠት አከበረው።
ከተማዪቱን፣ ንጉሧንና መንደሮቿን ይዘው በሰይፍ ስለት ፈጇቸው፤ በውስጧ ያለውንም ሁሉ አንድም ሳያስቀሩ ደመሰሱ፤ በልብናና በንጉሧ እንዲሁም በኬብሮን ያደረጉትን ሁሉ እዚህም በዳቤርና በንጉሧ ላይ ደገሙት።
ኢያሱ እነዚህን የነገሥታት ከተሞች በሙሉና ነገሥታታቸውን ሁሉ ያዘ፤ በሰይፍም ስለት ፈጃቸው፤ የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ ባዘዘውም መሠረት ፈጽሞ ደመሰሳቸው።
ሳኦልም ሳሙኤልን መልሶ እንዲህ አለው፤ “እግዚአብሔርን ታዝዣለሁ፤ እግዚአብሔር በላከኝ መሠረት ሄጃለሁ፤ አማሌቃውያንን በሙሉ አጥፍቼ ንጉሣቸውን አጋግን አምጥቻለሁ።
አሁንም ሂድ፤ አማሌቃውያንን ውጋ፤ ያላቸውንም ሁሉ ፈጽመህ አጥፋ፤ አንዱንም አታስቀር፤ ወንዱንና ሴቱን፣ ልጁንና ሕፃኑን፣ የቀንድ ከብቱንና በጉን፣ ግመሉንና አህያውን ግደል።’ ”
የካህናቱንም ከተማ ኖብን በሰይፍ መታት፣ በዚያ የሚኖሩትንም ወንዶችንና ሴቶችን፣ ልጆችንና ጡት የሚጠቡ ሕፃናትን፣ እንዲሁም በሬዎችንና አህያዎችን፣ በጎችንም ሁሉ በሰይፍ ስለት ፈጃቸው።
በሦስተኛው ቀን ዳዊትና ሰዎቹ ጺቅላግ ደረሱ፤ በዚህ ጊዜ አማሌቃውያን ደቡቡን አገርና ጺቅላግን ወረው ነበር፤ ጺቅላግንም ወግተው አቃጥለው ነበር።