1 ሳሙኤል 14:51 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሳኦል አባት ቂስና የአበኔር አባት ኔር ሁለቱም የአቢኤል ልጆች ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሳኦል አባት ቂስና የአበኔር አባት ኔር የአቢኤል ልጆች ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም የሳኦል አባት ቂስና የአበኔር አባት ኔር የአቢኤል ልጆች ነበሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሳኦልም አባት ቂስ ነበረ፤ የአቤኔርም አባት የአብኤል ልጅ የያሚን ልጅ ኔር ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሳኦልም አባት ቂስ ነበረ፥ የአበኔርም አባት ኔር የአቢኤል ልጅ ነበረ። |
ዳዊትም ተነሥቶ ሳኦል ወደ ሰፈረበት ቦታ ሄደ፤ ሳኦልና የሰራዊቱ አለቃ፣ የኔር ልጅ አበኔር የተኙበትን ስፍራ አየ። ሳኦል በሰፈሩ መካከል ተኝቶ ሳለ፣ ሰራዊቱ በዙሪያው ሰፍሮ ነበር።
ሳኦልም፣ “እኔ ከእስራኤል ነገዶች ውስጥ በጣም አነስተኛ ከሆነው ከብንያም ወገን አይደለሁምን? ጐሣዬስ ከብንያም ነገድ ጐሣዎች ሁሉ የሚያንስ አይደለምን? ታዲያ እንዲህ ያለውን ነገር ስለ ምን ትነግረኛለህ?” ብሎ መለሰለት።