ሩት 1:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አይሆንም! እኛ ከአንቺ ጋር ወደ ወገኖችሽ እንሄዳለን” አሉአት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀጥለውም፣ “አይሆንም! ከአንቺ ጋራ ተመልሰን ወደ ወገኖችሽ እንሄዳለን” አሏት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም፦ “ከአንቺ ጋር ወደ ሕዝብሽ እንመለሳለን” አሉአት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም፦ ከአንቺ ጋር ወደ ሕዝብሽ እንመለሳለን አሉአት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም “ከእንቺ ጋር ወደ ሕዝብሽ እንመለሳለን፤” አሉአት። |
በእነዚያ ቀኖች ዐሥር የሌላ አገር ሰዎች ወደ አንድ አይሁዳዊ ቀርበው የልብሱን ዘርፍ በመያዝ ‘እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር መሆኑን ስለ ሰማን ከእናንተ ጋር እንሂድ’ ይሉታል።”
ናዖሚም እንዲህ አለቻቸው፤ “ልጆቼ ሆይ! እባካችሁ ተመለሱ፤ ከእኔ ጋር ለመሄድ የምትፈልጉት ለምንድነው? ለእናንተ ባሎች የሚሆኑ ልጆች እንደገና መውለድ የምችል ይመስላችኋልን?
እያንዳንዳችሁ እንደገና ባል አግብታችሁ ትዳር እንድትመሠርቱ እግዚአብሔር ይርዳችሁ።” ከዚህ በኋላ ናዖሚ ለመሰናበት ሳመቻቸው፤ እነርሱ ግን ድምፃቸውን ከፍ አድርገው አለቀሱ።