ኢዮስያስ ግን ጦርነት ለመግጠም ቊርጥ ውሳኔ አደረገ፤ እግዚአብሔር በንጉሥ ኒካዑ አማካይነት የተናገረውንም ሊሰማ አልፈለገም፤ ልብሰ መንግሥቱን ለውጦ ሌላ ሰው በመምሰል በመጊዶ ወደሚገኘው ሜዳ ሊዋጋ ሄደ።
ራእይ 16:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መናፍስቱም ነገሥታቱን በዕብራይስጥ አርማጌዶን በሚባል ስፍራ ሰበሰቡአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም ነገሥታቱን በዕብራይስጥ አርማጌዶን በሚባል ስፍራ ሰበሰቧቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዕብራይስጥም አርማጌዶን ወደሚባል ስፍራ እስከተቱአቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዕብራይስጥም አርማጌዶን ወደሚባል ስፍራ እስከተቱአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዕብራይስጥም አርማጌዶን ወደሚባል ስፍራ እስከተቱአቸው። |
ኢዮስያስ ግን ጦርነት ለመግጠም ቊርጥ ውሳኔ አደረገ፤ እግዚአብሔር በንጉሥ ኒካዑ አማካይነት የተናገረውንም ሊሰማ አልፈለገም፤ ልብሰ መንግሥቱን ለውጦ ሌላ ሰው በመምሰል በመጊዶ ወደሚገኘው ሜዳ ሊዋጋ ሄደ።
ጲላጦስ ይህን በሰማ ጊዜ ኢየሱስን ወደ ውጪ አውጥቶ “ጠፍጣፋ ድንጋይ” በተባለው ስፍራ በፍርድ ወንበር ተቀመጠ፤ ይህ ስፍራ በዕብራይስጥ ቋንቋ “ገበታ” ይባላል።
በኢየሩሳሌም በበጎች በር አጠገብ፥ በዕብራይስጥ ቋንቋ ቤተ ሳይዳ የሚባል አንድ የምንጭ ኲሬ ነበረ፤ በዙሪያውም አምስት ከላይ ክዳን ያላቸው መተላለፊያዎች ነበሩ።
ሁላችንም በመሬት ላይ ወድቀን ሳለ በአይሁድ ቋንቋ ‘ሳውል! ሳውል! ስለምን ታሳድደኛለህ? በሰይፍ ስለት ላይ ብትቆም ራስህን ትጐዳለህ’ የሚል ድምፅ ሰማሁ።
እነርሱ በበጉ ላይ ጦርነት ይከፍታሉ፤ ነገር ግን በጉ የጌቶች ጌታና የነገሥታት ንጉሥ ስለ ሆነ ድል ይነሣቸዋል፤ ከእርሱ ጋር ያሉት የተጠሩ የተመረጡና የታመኑ ናቸው።”
የያቢን ሠራዊት አዛዥ የሆነው ሲሣራ በቂሾን ወንዝ አንተን ለመውጋት እንዲመጣ አደርጋለሁ፤ እርሱም ሠረገሎቹንና ወታደሮቹን አሰልፎ ይመጣል፤ እኔም በእርሱ ላይ ድልን እንድትቀዳጅ አደርግሃለሁ።’ ”