ሰማይና ምድር ደስ ይበላቸው! ባሕርና በውስጡ ያሉት ሁሉ እልል ይበሉ!
ሰማያት ደስ ይበላቸው፤ ምድርም ሐሤት ታድርግ፤ ባሕርና በውስጧ ያለው ሁሉ ያስተጋባ፤
ሰማያት ደስ ይበላቸው፥ ምድርም ሐሤትን ታድርግ፥ ባሕርና ሞላዋ ይናወጡ፥
ብርሃን ለጻድቃን፥ ደስታም ለልበ ቅኖች ወጣ።
ባሕርና በውስጡ ያሉት ሁሉ እልል ይበሉ! ማሳና በላይዋ የሚገኙ ሰብሎች ሁሉ ደስ ይበላቸው!
ሰማይና ምድር፥ ባሕሮችና በውስጣቸው የሚኖሩ ተንቀሳቃሽ ፍጥረቶች ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግኑት።
እግዚአብሔር ንጉሥ ነው! ምድር ሆይ ደስ ይበልሽ! እናንተ በባሕር ውስጥ ያላችሁ ደሴቶች ሁሉ፥ ደስ ይበላችሁ!
ሰማያት ሆይ! እግዚአብሔር ሕዝቡን እስራኤልን በማዳን ክብሩን ገልጦአልና በደስታ ዘምሩ፤ ምድርም ከታች እልል በዪ፤ ተራራዎች፥ ጫካዎችና በውስጣቸው የምትገኙ ዛፎች ሁሉ የደስታ ድምፅ እያሰማችሁ ፈንድቁ።
እግዚአብሔር ሕዝቡን ስለሚያጽናና እና ለሚሠቃዩትም ስለሚራራ ሰማያት ሆይ! ዘምሩ፤ ምድር ሆይ! ደስ ይበልሽ፤ ተራራዎች ሆይ! እልል በሉ።
ንስሓ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ ምክንያት በሰማይ በእግዚአብሔር መላእክት ዘንድ እንዲሁ ደስታ ይሆናል እላችኋለሁ።”
መልአኩ ግን እንዲህ አላቸው፦ “አትፍሩ! ለሕዝቡ ሁሉ ታላቅ ደስታ የሚሆን መልካም ዜና ይዤላችሁ መጥቻለሁ፤
ስለዚህ ሰማያትና በውስጣቸው የምትኖሩ ሁሉ ደስ ይበላችሁ! ጥቂት ጊዜ ብቻ እንደ ቀረው ስላወቀ ዲያብሎስ በታላቅ ቊጣ ወደ እናንተ ወርዶአልና ምድርና ባሕር ወዮላችሁ!”