እግዚአብሔር ሆይ! ከእኔ አትራቅ፤ ረዳቴ ሆይ! እኔን ለመርዳት ፈጥነህ ድረስ።
አንተ ግን፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ ከእኔ አትራቅ፤ ዐጋዤ ሆይ፤ እኔን ለመርዳት ፍጠን።
ልብሶቼን ለራሳቸው ተከፋፈሉ፥ በቀሚሴም ላይ ዕጣ ተጣጣሉ።
እግዚአብሔር ሆይ! ስለምን እንደዚህ ርቀህ ትቆማለህ? በችግር ጊዜስ ስለምን ትሰወራለህ?
እግዚአብሔር ሆይ! ኀይል የምትሰጠኝ አንተ ስለ ሆንክ፥ እወድሃለሁ።
አምላክ ሆይ! ኀይልን ስለ ሰጠኸው ንጉሥ ደስ ብሎታል፤ ድልን ስለ አቀዳጀኸውም ሐሴት ያደርጋል።
መከራ ሊደርስብኝ ስለ ተቃረበና የሚረዳኝም ስለሌለ እባክህ ከእኔ አትራቅ!
እግዚአብሔር ሆይ! እባክህ አድነኝ፤ እግዚአብሔር ሆይ! ፈጥነህ እርዳኝ።
አምላክ ሆይ! እኔ ችግረኛ ድኻ ነኝ፤ አንተ ግን አልረሳኸኝም፤ አንተ ረዳቴና አዳኜ ስለ ሆንክ አሁንም በፍጥነት እርዳኝ።
እኔ ጐስቋላና ምስኪን ነኝ፤ አምላክ ሆይ! ፈጥነህ ወደ እኔ ና፤ እግዚአብሔር ሆይ! ረዳቴና አዳኜ አንተ ስለ ሆንክ አትዘግይ!