መዝሙር 21:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ትውልዳቸውን ከምድር ላይ ታጠፋለህ፤ ዘራቸውንም ከሕዝቦች መካከል ለይተህ ትደመስሳለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዘራቸውን ከምድር፣ ዘር ማንዘራቸውንም ከሰው ልጆች መካከል ታጠፋለህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በተቈጣህም ጊዜ እንደ እሳት እቶን ታደርጋቸዋለህ፥ ጌታ በቁጣው ይውጣቸዋል፥ እሳትም ትበላቸዋለች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከማኅፀን ጀምሮ በአንተ ላይ ተጣልሁ፤ ከእናቴ ማኅፀን ጀምረህ አንተ አምላኬ ነህ። |
አንተ አገርህን አጥፍተህ፥ የገዛ ሕዝብህን ፈጅተሃል፤ ስለዚህም አንተ እንደ ሌሎች መንግሥታት መቃብር የማግኘት ዕድል አይኖርህም፤ ከክፉ ቤተሰብ መካከል የሚተርፍ ዘር አይኖርም።
የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፥ ትዕቢተኞችና ክፉ አድራጊዎች እንደ ገለባ በእሳት የሚቃጠሉበት ጊዜ እየመጣ ነው፤ የሚመጣውም ከእነርሱ ሥር፥ ወይም ቅርንጫፍ ሳያስቀር ሁሉንም ያቃጥላል።