ምሳሌ 28:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ክፉ ሰዎች ሲሾሙ ሰዎች ይደበቃሉ፤ እነርሱ ሲሻሩ ግን ጻድቃን ይበዛሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክፉዎች ሥልጣን በሚይዙ ጊዜ ሕዝብ ይሸሸጋል፤ ክፉዎች በሚጠፉበት ጊዜ ግን ጻድቃን ይበዛሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ክፉዎች በተነሡ ጊዜ ሰዎች ይሸሸጋሉ፥ እነርሱ በጠፉ ጊዜ ግን ጻድቃን ይበዛሉ። |
በየትኛውም አገርና በማንኛይቱም ከተማ የንጉሡ ዐዋጅ በተነበበበት ስፍራ ሁሉ በአይሁድ ዘንድ ተድላና ደስታ ሆነ፤ በዚሁ ምክንያት አይሁድን ከመፍራት የተነሣ ከሌሎች አሕዛብ ወገኖች ብዙዎቹ የአይሁድን ሃይማኖት ተቀበሉ።