Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢዮብ 24:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ድኾችን በመጸየፍ ከየመንገዱ ያባርራሉ፤ ከፊታቸውም ሸሽተው እንዲደበቁ ያደርጋሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ድኾችን ከመንገድ ያስወግዳሉ፤ የምድሪቱም ችግረኞችን ይሸሸጋሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ድሆቹን ከመንገድ ያስወጣሉ፥ የምድርም ችግረኞች ሁሉ ይሸሸጋሉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ደካ​ሞ​ችን ከእ​ው​ነት መን​ገድ ያወ​ጣሉ፤ የም​ድ​ርም የዋ​ሃን ሁሉ በአ​ን​ድ​ነት ይሸ​ሸ​ጋሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ድሆቹን ከመንገድ ያወጣሉ፥ የምድርም ችግረኞች ሁሉ ይሸሸጋሉ።

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 24:4
22 Referencias Cruzadas  

ነፍሰ ገዳይ ገና ሳይነጋ በማለዳ ተነሥቶ፥ ድኾችንና ችግረኞችን ይገድላል፤ በሌሊትም ለስርቆት ይሰማራል።


ይህም የሆነው የድኾችን ጩኸት ሰምቼ እታደጋቸውና፥ ወላጆቻቸው የሞቱባቸውንም ልጆች እረዳቸው ስለ ነበረ ነው።


ለድኾች አባት፥ ለማላውቃቸውም ሰዎች ጠበቃ ነበርኩ።


ለተቸገሩ ሰዎች አላለቀስኩምን? ለድኾችስ አልተጨነቅኹምን?


“ድኾች የሚለምኑትን ከልክዬ አላውቅም፤ ባሎቻቸው የሞቱባቸውንም ሴቶች ከማጽናናት አልተቈጠብኩም።


አንድ ሰው ከልብስ እጦት ወይም አንድ ችግረኛ የሚለብሰው አጥቶ ራቁቱን ሆኖ ባይ፥


ሰውየው ደግ ሥራ ለማድረግ ፈጽሞ አላሰበም፤ ድኾችን፥ ችግረኞችንና ምስኪኖችን እያሳደደ ይገድል ነበር።


ድኾችን የሚረዱ የተባረኩ ናቸው፤ እነርሱም በተቸገሩ ጊዜ እግዚአብሔር ይረዳቸዋል።


ድኾችን ማስጨነቅ ፈጣሪን መናቅ ነው፤ ለድኾች ቸርነትን ማድረግ ግን እግዚአብሔርን እንደ ማክበር ይቈጠራል።


ለሀብታሞች ስጦታ የሚሰጥ፥ ወይም ሀብት ለማግኘት ብሎ ድኾችን የሚጨቊን ሰው ይደኸያል።


ደጋግ ሰዎች ድል በሚያደርጉበት ጊዜ ሰው ሁሉ ይደሰታል፤ ክፉ ሰዎች ሥልጣን በሚይዙበት ጊዜ ግን ሰው ሁሉ በሐዘን አንገቱን ይደፋል።


ክፉ ሰዎች ሲሾሙ ሰዎች ይደበቃሉ፤ እነርሱ ሲሻሩ ግን ጻድቃን ይበዛሉ።


ጥርሳቸው እንደ ሰይፍ፥ መንጋጋቸው እንደ ካራ የሆኑ ድኾችንና ችግረኞችን በግፍ የሚበዘብዙ ሰዎች አሉ።


የድኾች መብት እንዳይከበርና የተበደሉ ፍትሕ እንዳያገኙ የምታደርጉበት ዘዴ ይኸው ነው፤ በዚሁ ዘዴ ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶችና አሳዳጊ የሌላቸውን የሙት ልጆች ንብረት ትነጥቃላችሁ።


ድኾችንና ችግረኞችን ቢያስጨንቅ፥ ቢቀማ፥ ገንዘብ ሲያበድር በመያዣ ስም የወሰደውን ቢያስቀር፥ በአሕዛብ መስገጃ ስፍራዎች ጣዖትን ቢያመልክ አጸያፊ ነገሮችን ቢያደርግ፥


አባቱ ግን ብዝበዛን ስለ ፈጸመ፥ ወንድሙን ስለ ቀማና በሕዝቡ ዘንድ መልካም ያልሆነውን ነገር ስላደረገ በበደሉ ይሞታል።


የሀገሪቱ ሰዎች ዝርፊያና ቅሚያ ያካሄዳሉ፤ ድኾችን፥ ችግረኞችንና መጻተኞችን ፍትሕ በመንሣት ይበድላሉ።


ደካሞችንና ረዳት የሌላቸውን በትቢያ ላይ ጥለው ራስ ራሳቸውን ይረግጣሉ፤ የተዋረዱ ምስኪኖችንም ገፍትረው ከመንገድ ያስወጣሉ፤ አባትና ልጅ ሁለቱም ከአንዲት ሴት ጋር ያመነዝራሉ፤ በዚህም ሥራቸው የተቀደሰውን ስሜን ያረክሳሉ።


እንደ ባሳን ቅልብ ላሞች ሰውነታችሁን ያወፈራችሁ የሰማርያ ሴቶች ሆይ! ይህን ቃል አድምጡ! እናንተ ደካሞችን ታዋርዳላችሁ፤ ድኾችን ትጨቊናላችሁ፤ ባሎቻችሁ ሁልጊዜ የሚያሰክር መጠጥ እንዲያቀርቡላችሁ ትጠይቃላችሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos