ነገር ግን ማረፊያው መልካም ምድሩም አስደሳች መሆኑን ባየ ጊዜ፥ ጭነቱን ለመሸከም ትከሻውን ዝቅ ያደርጋል፤ እንደ አገልጋይ ሆኖም ከባድ የጒልበት ሥራ ይሠራል።
ምሳሌ 2:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ እርስዋ ቤት ብታመራ ጒዞህ ወደ ሞት ይሆናል፤ ወደ እርስዋ መሄድ ወደ ሙታን ዓለም እንደ መውረድ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቤቷ ወደ ሞት ያደርሳል፤ መንገዷም ወደ መናፍስተ ሙታን ያመራል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቤትዋ ወደ ሞት ያዘነበለ ነው፥ አካሄድዋም ወደ ሙታን ጥላ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቤቷን በሞት አጠገብ አኖረች፥ አካሄድዋንም ከኀያላን ጋር ከምድር ወደ ሲኦል አቀናች። |
ነገር ግን ማረፊያው መልካም ምድሩም አስደሳች መሆኑን ባየ ጊዜ፥ ጭነቱን ለመሸከም ትከሻውን ዝቅ ያደርጋል፤ እንደ አገልጋይ ሆኖም ከባድ የጒልበት ሥራ ይሠራል።
አመንዝራም ቢሆን፥ ማናቸውንም የርኲሰት ሥራ የሚያደርግ ቢሆን፥ ወይም ጣዖት እንደ ማምለክ የሆነ ስግብግብነት ቢሆን፥ በክርስቶስና በእግዚአብሔር መንግሥት ርስት እንደማያገኝ ዕወቁ።
ነገር ግን ፈሪዎች፥ እምነተ ቢሶች፥ ርኩሶች፥ ነፍሰ ገዳዮች፥ አመንዝሮች፥ አስማተኞች፥ ጣዖት አምላኪዎች፥ ውሸታሞች ሁሉ ዕጣ ክፍላቸው በዲን በሚቃጠለው በእሳት ባሕር ውስጥ ይሆናል፤ ይህም ሁለተኛው ሞት ነው።”
እንደ ውሻ የሚልከፈከፉ፥ አስማተኞች፥ አመንዝሮች፥ ነፍሰ ገዳዮች፥ ጣዖት አምላኪዎች፥ ውሸትን የሚወዱና በሐሰት መንገድ የሚሄዱ ሁሉ ከከተማይቱ ውጪ ይሆናሉ።