ምሳሌ 19:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሐሰት የሚመሰክር ሰው ሳይቀጣ አይቀርም፤ ሐሰትንም የሚናገር ጥፋት ያገኘዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሐሰተኛ ምስክር ከቅጣት አያመልጥም፤ ውሸት የሚነዛም ይጠፋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሐሰተኛ ምስክር ሳይቀጣ አይቀርም፥ በሐሰትም የሚናገር ይጠፋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሐሰተኛ ምስክር ከቅጣት አይድንም፤ ክፋትን የሚያቀጣጥላትም ይጠፋባታል። |
“እኔ ተስፋ ያላስቈረጥኳቸውን ጻድቃንን ሐሰት በመናገር ተስፋ አስቈርጣችኋል፤ ክፉዎች ሕይወታቸውን ለማዳን ከኃጢአታቸው እንዳይመለሱ አደፋፍራችኋል።
ከዚህም በኋላ ዳንኤልን የከሰሱት ሰዎች ተይዘው እንዲመጡ ንጉሡ አዘዘ፤ እነርሱም ተይዘው ከሚስቶቻቸውና ከልጆቻቸው ጋር በአንበሶች ጒድጓድ ውስጥ እንዲጣሉ አደረገ፤ ገና ወደ ጒድጓዱ አዘቅት ሳይደርሱም አንበሶቹ ቦጫጨቋቸው፤ አጥንቶቻቸውንም ሁሉ ሰባበሩ።
ነገር ግን አውሬው ተያዘ፤ ከእርሱም ጋር በፊቱ ብዙ ተአምራት ያደርግ የነበረው ሐሰተኛው ነቢይ ተያዘ፤ እርሱ የአውሬው ምልክት የነበረባቸውንና ለአውሬውም ምስል ይሰግዱ የነበሩትን ተአምራት እያደረገ ያስታቸው ነበር፤ እነዚህ ሁለቱ በዲን ወደሚቃጠለው የእሳት ባሕር ከነሕይወታቸው ተጣሉ።
ነገር ግን ፈሪዎች፥ እምነተ ቢሶች፥ ርኩሶች፥ ነፍሰ ገዳዮች፥ አመንዝሮች፥ አስማተኞች፥ ጣዖት አምላኪዎች፥ ውሸታሞች ሁሉ ዕጣ ክፍላቸው በዲን በሚቃጠለው በእሳት ባሕር ውስጥ ይሆናል፤ ይህም ሁለተኛው ሞት ነው።”
እንደ ውሻ የሚልከፈከፉ፥ አስማተኞች፥ አመንዝሮች፥ ነፍሰ ገዳዮች፥ ጣዖት አምላኪዎች፥ ውሸትን የሚወዱና በሐሰት መንገድ የሚሄዱ ሁሉ ከከተማይቱ ውጪ ይሆናሉ።