ከዚህ በፊት ለንጉሠ ነገሥት አርጤክስስ ባስረዳሁት ጊዜ “አምላካችን እግዚአብሔር በእርሱ የሚታመኑትን ሁሉ ይባርካል፤ እርሱን የሚተዉትን ግን በብርቱ ይቀጣቸዋል” በማለት ገልጬለት ስለ ነበረ በመንገድ ከሚገጥሙን ጠላቶቻችን እንዲጠብቁን ወታደሮችንና ፈረሰኞችን ይሰጠን ዘንድ ንጉሡን ጠይቄው ቢሆን ኖሮ ባፈርኩ ነበር።
ነህምያ 2:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሠ ነገሥቱም ጥቂት የጦር መኰንኖችና ፈረሰኞች ከእኔ ጋር እንዲሄዱ አደረገ፤ እኔም ከኤፍራጥስ በስተ ምዕራብ ወደሚገኘው ክፍለ ሀገር ጒዞዬን ቀጠልኩ፤ እዚያ እንደ ደረስኩም ደብዳቤዎቹን ለአገረ ገዢዎቹ አስረከብኩ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ በኤፍራጥስ ማዶ ወደሚገኙት አገረ ገዦች ሄጄ የንጉሡን ደብዳቤዎች ሰጠኋቸው፤ ንጉሡም የጦር አለቆችና ፈረሰኞች ዐብረውኝ እንዲሄዱ አድርጎ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በወንዙ ማዶ ወዳሉት ገዢዎች ሄጄ የንጉሡን ደብዳቤዎች ሰጠኋቸው። ንጉሡ ከእኔ ጋር የጦር አለቆችና ፈረሰኞች ልኮ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በወንዙም ማዶ ወዳሉት ሀገረ ገዦች መጥቼ የንጉሡን ደብዳቤዎች ሰጠኋቸው። ንጉሡም ከእኔ ጋር የሠራዊቱን አለቆችና ፈረሰኞች ልኮ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በወንዙም ማዶ ወዳሉት አለቆች መጥቼ የንጉሡን ደብዳቤ ሰጠኋቸው። ንጉሡም ከእኔ ጋር የሠራዊቱን አለቆችና ፈረሰኞች ሰደደ። |
ከዚህ በፊት ለንጉሠ ነገሥት አርጤክስስ ባስረዳሁት ጊዜ “አምላካችን እግዚአብሔር በእርሱ የሚታመኑትን ሁሉ ይባርካል፤ እርሱን የሚተዉትን ግን በብርቱ ይቀጣቸዋል” በማለት ገልጬለት ስለ ነበረ በመንገድ ከሚገጥሙን ጠላቶቻችን እንዲጠብቁን ወታደሮችንና ፈረሰኞችን ይሰጠን ዘንድ ንጉሡን ጠይቄው ቢሆን ኖሮ ባፈርኩ ነበር።
ከዚያም በመቀጠል ወደ ይሁዳ ማለፍ እንዲፈቅዱልኝ ከኤፍራጥስ ወንዝ በስተ ምዕራብ በሚገኘው ክፍለ ሀገር ላሉት አገረ ገዢዎች የይለፍ ደብዳቤ እንዲሰጠኝ ለንጉሠ ነገሥቱ ልመና አቀረብኩ፤