ማቴዎስ 12:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰዎቹን ግን ስለ እርሱ ለማንም እንዳይናገሩ አዘዛቸው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ማንነቱን ለማንም እንዳይናገሩ አዘዛቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዳያጋልጡትም አዘዛቸው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በነቢዩ በኢሳይያስ የተባለው ይፈጸም ዘንድ እንዲህ ሲል መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በነቢዩ በኢሳይያስ የተባለው ይፈጸም ዘንድ እንዲህ ሲል፦ |
ከዚህ በኋላ ኢየሱስ፥ ከለምጹ የዳነውን ሰው እንዲህ አለው፤ “ይህን ነገር ለማንም አትናገር፤ ነገር ግን ሄደህ መዳንህን ለካህን አሳይ፤ ምስክር ይሆንባቸው ዘንድ፥ ስለ መዳንህ ሙሴ ያዘዘውን መባ ለእግዚአብሔር አቅርብ” አለው።