ሉቃስ 9:49 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በኋላ ዮሐንስ ኢየሱስን፥ “መምህር ሆይ፥ አንድ ሰው በስምህ አጋንንት ሲያወጣ አየነው፤ ነገር ግን ከእኛ ጋር ስላልሆነ ከለከልነው፤” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዮሐንስም፣ “ጌታ ሆይ፤ አንድ ሰው በስምህ አጋንንት ሲያወጣ አየነው፤ ከእኛ ጋራ ሆኖ ስለማይከተል ልንከለክለው ሞከርን” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዮሐንስም መልሶ፦ “አቤቱ! አንድ ሰው በስምህ አጋንንትን ሲያወጣ አየነው፤ ከእኛ ጋርም ስለማይከተል ከለከልነው” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮሐንስም መልሶ፥ “መምህር ሆይ፥ በስምህ ጋኔን ሲያወጣ ያየነው አንድ ሰው አለ፤ ከእኛም ጋር አልተከተለህምና ከለከልነው፤” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዮሐንስም መልሶ፦ አቤቱ፥ አንድ ሰው በስምህ አጋንንትን ሲያወጣ አየነው፥ ከእኛ ጋርም ስለማይከተል ከለከልነው አለው። |
ሁለቱ ሰዎች ከኢየሱስ ተለይተው በሄዱ ጊዜ ጴጥሮስ ኢየሱስን “መምህር ሆይ፥ እዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ስለዚህ አንድ ለአንተ፥ አንድ ለሙሴ፥ አንድ ለኤልያስ የሚሆኑ ሦስት ዳሶች እንሥራ!” አለው፤ ጴጥሮስ ይህን ሲናገር የሚለውን አያውቅም ነበር።
“የኢየሱስን ስም በመጥራት እንዳታስተምሩ በጥብቅ አዘናችሁ ነበር፤ ነገር ግን እነሆ፥ ኢየሩሳሌምን በትምህርታችሁ ሞላችኋት፤ እናንተ ለዚያ ሰው ሞት እኛን ተጠያቂዎች ልታደርጉን ትፈልጋላችሁ።”
አሕዛብ የሚድኑበትን ቃል እንዳንናገር እንኳ ይከለክሉናል፤ በዚህ ዐይነት ኃጢአትን በኃጢአት ላይ እየጨመሩ ይሄዳሉ፤ ስለዚህ በመጨረሻ የእግዚአብሔር ቊጣ መጥቶባቸዋል።