ሉቃስ 9:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደቀ መዛሙርቱም ልክ እርሱ እንዳዘዛቸው ሰዎቹን እንዲቀመጡ አደረጉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደቀ መዛሙርቱም በታዘዙት መሠረት ሰዎቹ እንዲቀመጡ አደረጉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህም አደረጉና ሁሉንም አስቀመጡአቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲሁም አደረጉ፤ ሁሉም ተቀመጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህም አደረጉ ሁሉንም አስቀመጡአቸው። |
ከዚህም በኋላ ኢየሱስ አምስቱን እንጀራና ሁለቱን ዓሣ ይዞ ወደ ሰማይ አሻቅቦ አየና እግዚአብሔርን አመሰገነ፤ ቈርሶም ለሰዎቹ እንዲያድሉ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠ፤