ሉቃስ 8:45 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስም “ማን ነው የነካኝ?” ሲል ጠየቀ። ሁሉም “እኛ አልነካንህም፤” አሉ፤ ጴጥሮስም “መምህር ሆይ፥ ሕዝቡ እየተጋፋ ሲከተልህ እያየህ ማን ነው የነካኝ ትላለህን?” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስም፣ “የነካኝ ማን ነው?” አለ። ሁሉም መንካታቸውን በካዱ ጊዜ ጴጥሮስ፣ “ጌታ ሆይ፤ ሕዝቡ ሁሉ ከብቦህ በግፊያ እያስጨነቀህ ነው” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢየሱስም፦ “ማን ነው የነካኝ?” አለ። ሁሉም በካዱ ጊዜ፥ ጴጥሮስ፦ “አቤቱ! ሕዝቡ በዙሪያህ ከበውህ እየተጋፉህ እኮ ነው!” አለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌታችን ኢየሱስም፥ “ማን ዳሰሰኝ?” አለ፤ ሁሉም ካዱ፤ ጴጥሮስና ከእርሱ ጋር የነበሩትም፥ “መምህር ሆይ፥ ሰው ይጋፋህና ያጨናንቅህ የለምን? አንተ ግን ማን ዳሰሰኝ? ትላለህ” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢየሱስም፦ የዳሰሰኝ ማን ነው? አለ። ሁሉም በካዱ ጊዜ፥ ጴጥሮስና ከእርሱ ጋር የነበሩት፦ አቤቱ፥ ሕዝቡ ያጫንቁሃልና ያጋፉህማል፤ የዳሰሰኝ ማን ነው ትላለህን? አሉ። |
ኢየሱስ ግን “እናንተ ራሳችሁ የሚበሉትን ስጡአቸው፤” አላቸው። እነርሱም “እኛ ያለን አምስት እንጀራና ሁለት ዓሣ ብቻ ነው፤ ስለዚህ ሄደን ምግብ ካልገዛን በቀር ለዚህ ሁሉ ሕዝብ አይበቃም፤” አሉት።