ሉቃስ 12:59 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መቀጮህን ሁሉ ጨርሰህ ሳትከፍል ከእስር ቤት መውጣት እንደማትችልም እነግርሃለሁ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እልሃለሁ፤ የመጨረሻዋን ሳንቲም እስክትከፍል ድረስ ከዚያ አትወጣም።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የመጨረሻዋን ግማሽ ሳንቲም እስክትከፍል ድረስ ከዚያ ከቶ አትወጣም።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያለብህን የመጨረሻዋን ግማሽ ሣንቲም ቢሆን እስክትጨርስ ድረስ አትወጣም እልሃለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እልሃለሁ፥ የመጨረሻዋን ግማሽ ሳንቲም እስክትከፍል ድረስ ከዚያ ከቶ አትወጣም። |
ከዚህ በኋላ በግራው በኩል ያሉትንም እንዲህ ይላቸዋል፤ ‘እናንተ የተረገማችሁ! ከእኔ ወዲያ ራቁ! ለዲያብሎስና ለተከታዮቹ መላእክት ወደ ተዘጋጀው ወደ ዘለዓለም እሳት ሂዱ!
ከዚህም ሁሉ በላይ በእኛና በእናንተ መካከል ትልቅ ገደል አለ፤ ስለዚህ ከእኛ ወደ እናንተ፥ ከእናንተም ወደ እኛ መሻገር የሚችል ማንም የለም።’
ወንድሞች ሆይ! በእናንተ ምክንያት እግዚአብሔርን ሁልጊዜ እናመሰግናለን፤ ማመስገንም ተገቢያችን ነው፤ የምናመሰግነውም እምነታችሁ ይበልጥ እያደገና የእያንዳንዳችሁ የእርስ በርስ ፍቅር እየጨመረ በመሄዱ ነው።