La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሰቈቃወ 4:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ቀደም ብለው ምርጥ ምግብ ይመገቡ የነበሩት፥ አሁን በመንገድ ላይ ወድቀዋል። ሐምራዊ ልብስ ለብሰው ያደጉት አሁን በዐመድ ክምር ላይ ተጋደሙ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ምርጥ ምግብ ይበሉ የነበሩ፣ ተቸግረው በየመንገዱ ላይ ተንከራተቱ፤ ሐምራዊ ግምጃ ለብሰው ያደጉ፣ አሁን በዐመድ ክምር ላይ ተኙ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሄ። የጣፈጠ ነገር ይበሉ የነበሩ በመንገድ ጠፉ፥ በቀይ ግምጃ ያድጉ የነበሩ የፍግ ክምር አቀፉ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሄ። የጣ​ፈጠ ነገር ይበሉ የነ​በሩ በመ​ን​ገድ ጠፉ፤ በቀይ ግምጃ ያድጉ የነ​በሩ የፍግ ክምር አቀፉ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሄ። የጣፈጠ ነገር ይበሉ የነበሩ በመንገድ ጠፉ፥ በቀይ ግምጃ ያድጉ የነበሩ የፍግ ክምር አቀፉ።

Ver Capítulo



ሰቈቃወ 4:5
17 Referencias Cruzadas  

“የእስራኤል ሴቶች ሆይ! ውድ የሆነ ሐምራዊ ቀሚስ ያለብሳችሁ ለነበረው በወርቀ ዘቦም ላስጌጣችሁ፥ ለሳኦል አልቅሱለት!


እርሱም “የአሦር ንጉሠ ነገሥት ይህን ሁሉ ለእናንተና ለንጉሣችሁ ብቻ እንድናገር የላከኝ መሰላችሁን? ከቶ አይደለም፤ ልክ እንደ እናንተ ኩሳቸውን ለመብላትና ሽንታቸውን ለመጠጣት የሚገደዱ ሰዎችም ጭምር ስለ ሆኑ፥ እኔ የምናገረውን በቅጽሩ ላይ ያሉት ሰዎች ሁሉ እንዲሰሙት ነው” ሲል መለሰላቸው።


በተራራ ላይ በሚዘንበው ዝናብ ሰውነታቸው ይረሰርሳል፤ መጠለያም አጥተው ቋጥኝ ተጠግተው ያድራሉ።


ቤተሰብዋ በሙሉ ሞቃት ልብስ ስላለው በረዶ እንኳ ቢዘንብ አትሠጋም።


ሕዝብዋ ምግብ ማግኘት ፈልገው ይቃትታሉ፤ በሕይወት ለመኖር ሲሉ ሀብታቸውን ሁሉ በምግብ ይለውጣሉ፤ የኢየሩሳሌም ሕዝብ “እግዚአብሔር ሆይ! ተመልከተን! ውርደታችንን ሁሉ እይልን!” እያሉ ይጮኻሉ።


ዐሣማዎቹ ከሚመገቡት ብጣሪ ዐሠር ሆዱን ለመሙላት ይመኝ ነበር፤ ግን ይህንኑ እንኳ የሚሰጠው አልነበረም።


ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “ቀይ ከፋይና ቀጭን ልብስ የሚለብስ አንድ ሀብታም ሰው ነበር፤ እርሱም በየቀኑ በቅንጦት ይኖር ነበር።


ደግሞስ ምን ለማየት ወጣችሁ? የተዋበ ልብስ የለበሰውን ሰው ለማየት ነውን? የተዋበ ልብስ የሚለብሱና በድሎት የሚኖሩማ በነገሥታት ቤት ይገኛሉ፤


የዚህን ዓለም ደስታ ብቻ የምትወድ መበለት ግን በቁሟ የሞተች ናት።