ልክ በዚያኑ ጊዜ የያዕቆብ ልጆች ከተሰማሩበት መጡ፤ ስለ ተፈጸመው ድርጊት በሰሙ ጊዜ እጅግ ደነገጡ፤ ይህ ነገር መደረግ ስላልነበረበት ሴኬም የያዕቆብን ልጅ በመድፈር የእስራኤልን ሕዝብ በማዋረዱም እጅግ ተቈጡ።
ኢያሱ 7:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርም የሆኑ (የተከለከሉ) ነገሮች የተገኙበትም ሰው የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ስላፈረሰና በእስራኤል ላይ በደል ስለ ፈጸመ እርሱና የእርሱ የሆነ ሁሉ በእሳት ይቃጠል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዕርሙ የተገኘበት ሰው፣ እርሱና ያለው ሁሉ በእሳት ይቃጠላል፤ የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን አፍርሷል፤ በእስራኤልም ዘንድ አሳፋሪ ተግባር ፈጽሟልና።’ ” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርም የሆነውም ነገር የተገኘበት ሰው የጌታን ቃል ኪዳን አፍርሶአልና፥ በእስራኤልም ዘንድ በደል ፈጽሟልና እርሱና የእርሱ የሆነው ነገር ሁሉ በእሳት ይቃጠል።’ ” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምልክት የታየበት ሰው የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን አፍርሶአልና፥ በእስራኤልም ዘንድ በደል አድርጎአልና፥ እርሱና ያለው ሁሉ በእሳት ይቃጠላሉ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርም የሆነውም ነገር የተገኘበት ሰው የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን አፍርሶአልና፥ በእስራኤልም ዘንድ በደል አድርጎአልና እርሱና ያለው ሁሉ በእሳት ይቃጠላሉ። |
ልክ በዚያኑ ጊዜ የያዕቆብ ልጆች ከተሰማሩበት መጡ፤ ስለ ተፈጸመው ድርጊት በሰሙ ጊዜ እጅግ ደነገጡ፤ ይህ ነገር መደረግ ስላልነበረበት ሴኬም የያዕቆብን ልጅ በመድፈር የእስራኤልን ሕዝብ በማዋረዱም እጅግ ተቈጡ።
እንደዚህ ካዋረድከኝ በኋላ በሕዝብ ፊት ራሴን ቀና አድርጌ ለመሄድ እንዴት እችላለሁ? አንተም ብትሆን በእስራኤል እጅግ የተዋረድክ ትሆናለህ፤ ይልቅስ ለንጉሡ ብትነግረው እኔን ለአንተ በሚስትነት እንደሚሰጥህ እርግጠኛ ነኝ” አለችው።
እስራኤላውያን በድለዋል፤ እንዲጠብቁት ያዘዝኳቸውንም ቃል ኪዳን አፍርሰዋል፤ ከተከለከሉት ነገሮች ወስደዋል፤ ሰርቀዋል፤ ከራሳቸው ንብረት ጋር በማቀላቀል አታላዮች ሆነዋል።
በእስራኤል ላይ በፈጸሙት አሳፋሪ ተግባር በብንያም ግዛት የምትገኘውን የጊብዓን ሕዝብ ለመበቀል ለሚዘምተው ሠራዊት ስንቅ ያቀብሉ ዘንድ ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ መካከል ከመቶ ዐሥር፥ ከሺህ መቶ፥ ከዐሥር ሺህ አንድ ሺህ ሰው እንመድባለን።”
የጊብዓ ሰዎች በእኔ ላይ አደጋ ለመጣል መጥተው በሌሊት ቤቱን ከበቡት፤ በመጀመሪያ እኔን ለመግደል አስበው ነበር፤ በኋላ ግን በቊባቴ ላይ ተረባርበው ስላመነዘሩባት ሞተች፤
ከዚህ በኋላ የቁባቴን አስከሬን ወስጄ ቈራረጥሁት፤ እነርሱ ይህን የመሰለ ክፉ በደል ስለ ሠሩ የቈራረጥኋቸውን ቊርጥራጮች ወደ እስራኤል አገር ሁሉ ላክሁ።
ሳኦልም “በእርግጥ ተሳስቻለሁ፤ ልጄ ዳዊት ሆይ! ተመልሰህ ወደ እኔ ና፤ ዳግመኛ ልጐዳህ ከቶ አልፈልግም፤ በዛሬይቱ ሌሊት ሕይወቴን አትርፈሃል፤ እኔ እንደ ሞኝ ሆኜአለሁ! ከባድ የሆነ ስሕተትም ፈጽሜአለሁ!” ሲል መለሰ።