የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙት ሰዎች ስድስት እርምጃ በተራመዱ ቊጥር ዳዊት እንደገና እያስቆመ አንድ ወይፈንና አንድ የሰባ ፍሪዳ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ያቀርብ ነበር።
ኢያሱ 3:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሚከተለውን ትእዛዝ ሰጡ፦ “የሌዊ ዘር የሆኑት ካህናት የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት ተሸክመው ሲነሡ በምታዩበት ጊዜ፥ ሰፈሩን ለቃችሁ እነርሱን ተከተሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕዝቡንም እንዲህ ሲሉ አዘዙ፤ “ሌዋውያን ካህናቱ የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት ተሸክመው ስታዩ፣ ከሰፈራችሁ ተነሥታችሁ ታቦቱን ተከተሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕዝቡንም እንዲህ ብለው አዘዙ፦ “የአምላካችሁን የጌታን ቃል ኪዳን ታቦቱንና ሌዋውያን ካህናት ተሸክመውት ባያችሁ ጊዜ፥ ከሰፈራችሁ ተነስታችሁ እርሱን በመከተል፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለሕዝቡም እንዲህ ብለው ዐወጁ፥ “የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳኑን ታቦት ሌዋውያንና ካህናት ተሸክመውት ባያችሁ ጊዜ፥ ከሰፈራችሁ ተነሥታችሁ ተከተሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕዝቡን፦ የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦትና ሌዋውያን ካህናት ተሸክመውት ባያችሁ ጊዜ፥ ከሰፈራችሁ ተነስታችሁ ተከተሉት። |
የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙት ሰዎች ስድስት እርምጃ በተራመዱ ቊጥር ዳዊት እንደገና እያስቆመ አንድ ወይፈንና አንድ የሰባ ፍሪዳ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ያቀርብ ነበር።
እነርሱም የቃል ኪዳኑን ታቦት በኮረብታ ላይ ከሚገኘው ከአቢናዳብ ቤት አውጥተው በአዲስ ሠረገላ ላይ አኖሩት፤ ዑዛና አሕዮ ተብለው የሚጠሩት የአቢናዳብ ልጆች ሠረገላውን እየመሩ በሚጓዙበት ጊዜ፥
ሕዝቡ የተቀደሰው ተራራ ያለበትን የሲናን ምድረ በዳ ትተው የሦስት ቀን መንገድ ተጓዙ፤ የእግዚአብሔርም ቃል ኪዳን ታቦት የሚሰፍሩበትን ቦታ ለመፈለግ በፊታቸው ተጓዘ።
ከሰፈር በሚነሡበትም ጊዜ አሮንና ልጆቹ ንዋያተ ቅድሳቱንና የእነርሱንም መገልገያ ዕቃዎች ሁሉ ከሸፈኑ በኋላ የቀዓት ልጆች መጥተው ይሸከሙአቸው፤ ነገር ግን እንዳይሞቱ ንዋያተ ቅድሳቱን መንካት አይገባቸውም፤ እንግዲህ የመገናኛው ድንኳን በሚነሣበት ጊዜ ሁሉ የቀዓት ልጆች ኀላፊነት ይህ ነው።
ከዚያ በኋላ ሙሴ የእግዚአብሔርን ሕግ ጽፎ የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ታቦት አገልጋዮች ለሆኑት ለሌዋውያን ካህናትና ለእስራኤል ሕዝብ አለቆች ሰጣቸው።
ከዚህ በፊት ይህን ቦታ ስለማታውቁት የምትሄዱበትን መንገድ እነርሱ ያሳዩአችኋል፤ ነገር ግን ወደ ቃል ኪዳኑ ታቦት አትቅረቡ፤ በእናንተና በቃል ኪዳኑ ታቦት መካከል የሚኖረው ርቀት አንድ ኪሎ ሜትር ያኽል ይሁን።”
የቃል ኪዳኑን ታቦት ለሚሸከሙት ካህናት፦ ‘ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ ዳርቻ በምትደርሱበት ጊዜ በወንዙ ውስጥ ቀጥ ብላችሁ ቁሙ’ ብለህ ንገራቸው።”
ለሕዝቡ እንዲነግር እግዚአብሔር ኢያሱን ባዘዘው መሠረት ሁሉ ነገር እስኪፈጸም ድረስ ካህናቱ በዮርዳኖስ ወንዝ መካከል እንደ ቆሙ ቈዩ፤ ሙሴም ኢያሱን ያዘዘው ይህንኑ ነበር፤ ሕዝቡም ፈጥኖ ወንዙን ተሻገሩ።
እነርሱ ድንግሎች ስለ ሆኑ ከሴቶች ጋር ግንኙነት በማድረግ አልረከሱም፤ በጉ ወደሚሄድበትም ሁሉ ይከተሉታል። እነርሱ ለእግዚአብሔርና ለበጉ ከሰዎች መካከል እንደ በኲራት የቀረቡ ናቸው።
ሌዋውያንም የእግዚአብሔርን ታቦትና ከእርሱ ጋር የነበረውን ወርቅ የሞላበት ሣጥን አንሥተው በታላቁ ቋጥኝ ላይ አስቀመጡ፤ የቤትሼሜሽም ሰዎች የሚቃጠልና ሌላውንም መሥዋዕት ሁሉ ለእግዚአብሔር አቀረቡ፤