እርሱም ቃጣት፥ ናህላል፥ ሺምሮን፥ ይዳላና ቤተልሔም ተብለው የሚጠሩትን ዐሥራ ሁለት ከተሞችና በዙሪያቸው ያሉትን ታናናሽ ከተሞች ያጠቃልላል፤
ኢያሱ 19:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም እነዚህ ታላላቅና ታናናሽ ከተሞች ለዛብሎን ነገድ በየወገናቸው የተሰጡ ርስቶች ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነዚህ ሁሉ ለዛብሎን ነገድ ርስት ሆነው ለየጐሣ ለየጐሣው የተደለደሉ ከተሞችና መንደሮቻቸው ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዛብሎን ልጆች ርስት በየወገኖቻቸው እነዚህ ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዛብሎን ልጆች ነገድ ርስት በየወገኖቻቸው እነዚህ ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዛብሎን ልጆች ርስት በየወገኖቻቸው እነዚህ ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው። |
እርሱም ቃጣት፥ ናህላል፥ ሺምሮን፥ ይዳላና ቤተልሔም ተብለው የሚጠሩትን ዐሥራ ሁለት ከተሞችና በዙሪያቸው ያሉትን ታናናሽ ከተሞች ያጠቃልላል፤