ቀድሞ የእስራኤል ይዞታ የነበረውን በስተ ሰሜን ከሐማት መተላለፊያ ጀምሮ በስተ ደቡብ እስከ ሙት ባሕር የሚገኘውን ግዛት ሁሉ ድል ነሥቶ እንደገና አስመለሰ፤ ይህም ሁሉ የተፈጸመው በጋትሔፌር ተወላጅ አገልጋይ በሆነው በአሚታይ ልጅ በነቢዩ ዮናስ አማካይነት የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር በሰጠው የተስፋ ቃል መሠረት ነው።
ኢያሱ 19:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንደገናም በዚሁ በምሥራቅ በኩል ወደ ሪሞን በሚወስደው መንገድ ወደ ኔዓ አቅጣጫ ይታጠፍና ወደ ጋትሔፌርና ወደ ዒትቃጺን ይዘልቃል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ወደ ምሥራቅ በመቀጠል፣ ወደ ጋትሔፌርና ወደ ዒትቃጺን ይዘልቃል፤ ከዚያ ደግሞ ወደ ሪሞን በመሄድ ወደ ኒዓ ይታጠፋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም በምሥራቅ በኩል ወደ ጋት-ሔፍርና ወደ ዒታ-ቃጺን አለፈ፤ ወደ ሪምን በመውጣት ወደ ኒዓ ታጠፈ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚያም ወደ ጌቤሮ ምሥራቅ ወደ ከታሤም ከተማ ያልፋል፤ ወደ ሪናሞን ወደ ማታርዮዛ ይወጣል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ዳብራትም ወጣ፥ ወደ ያፊዓም ደረሰ፥ ከዚያም በምሥራቅ በኩል ወደ ጋትሔፍርና ወደ ዒታቃጺን አለፈ፥ ወደ ሪምንና ወደ ኒዓ ወጣ። |