ዮሐንስ 7:40 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ከሕዝቡ አንዳንዶቹ ይህን ቃል በሰሙ ጊዜ፦ “ይመጣል የተባለው ነቢይ በእርግጥ ይህ ነው” አሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሕዝቡ አንዳንዶቹ ቃሉን ሰምተው፣ “ይህ ሰው በርግጥ ነቢዩ ነው” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ከሕዝቡ አያሌ ሰዎች ይህን ቃል ሲሰሙ “ይህ በእውነት ነቢዩ ነው፤” አሉ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሕዝቡም ብዙ ሰዎች ይህን ነገር ሰምተው “በእውነት ይህ ነቢይ ነው” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ ከሕዝቡ አያሌ ሰዎች ይህን ቃል ሲሰሙ፦ “ይህ በእውነት ነቢዩ ነው” አሉ፤ |
እነርሱም “ታዲያ አንተ ማን ነህ? ኤልያስ ነህን?” ሲሉ ጠየቁት። እርሱም “አይደለሁም” ሲል መለሰላቸው። እነርሱም “ይመጣል የተባለው ነቢይ ነህን?” አሉት። እርሱም “አይደለሁም” አለ።
ሕዝቡም ስለ እርሱ በሹክሹክታ ይነጋገሩ ነበር፤ አንዳንዶቹ “እርሱ ደግ ሰው ነው” ሲሉ፥ ሌሎች ደግሞ “አይደለም፤ እርሱ ሕዝቡን ያስታል” ይሉ ነበር።