ኢዩኤል 3:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ቀን ፀሐይና ጨረቃ ይጨልማሉ፤ ከዋክብትም ብርሃናቸውን ያጣሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፀሓይና ጨረቃ ይጨልማሉ፤ ከዋክብትም ከእንግዲህ አያበሩም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፀሐይና ጨረቃ ጨልመዋል፥ ከዋክብትም ብርሃናቸውን ሰውረዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፀሐይና ጨረቃ ይጨልማሉ፤ ከዋክብትም ብርሃናቸውን ይሰውራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፀሐይና ጨረቃ ጨልመዋል፥ ከዋክብትም ብርሃናቸውን ሰውረዋል። |
“ከነዚያ ከመከራ ቀኖች በኋላ ወዲያውኑ ፀሐይ ትጨልማለች፤ ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም፤ ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ፤ የሰማያት ኀይሎችም ይናወጣሉ።
አራተኛው መልአክ መለከቱን ነፋ፤ የፀሐይ አንድ ሦስተኛ፥ የጨረቃ አንድ ሦስተኛ፥ የኮከቦች አንድ ሦስተኛ ተመታ፤ ስለዚህ የእነርሱ አንድ ሦስተኛቸው ጨለመ፤ በዚህ ዐይነት የቀን አንድ ሦስተኛና የሌሊት አንድ ሦስተኛ ያለ ብርሃን ሆነ።