ኢዮብ 4:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጹሕ ሰው ሆኖ መከራ የደረሰበት፥ ቀጥተኛ ሰው ሆኖ ሳለ የተደመሰሰ እንዳለ እስቲ አስብ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አሁንም አስተውል፤ ንጹሕ ሆኖ የጠፋ ማን ነው? ቅኖችስ መች ተደምስሰው ያውቃሉ? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እባክህ አስብ፥ ንጹሕ ሆኖ የጠፋ ማን ነው? ከልበ ቅንስ የተደመሰሰ ማን ነው? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እባክህ አስብ፥ ንጹሕ ሆኖ የጠፋ ማን ነው? ከጻድቃንስ የተደመሰሰ ማን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እባክህ አስብ፥ ንጹሕ ሆኖ የጠፋ ማን ነው? ከልበ ቅንስ የተደመሰሰ ማን ነው? |
የማልታ ሰዎች እባብ በጳውሎስ እጅ ላይ ተንጠልጥሎ ባዩ ጊዜ “ይህ ሰው በእርግጥ ነፍሰ ገዳይ ነው! ከባሕሩ ማዕበል በደኅና ቢወጣም ከአምላክ ፍርድ አምልጦ በሕይወት ለመኖር አልቻለም” ተባባሉ።
እንግዲህ ይህ ሁሉ እንዲህ ከሆነ ጌታ እርሱን በማምለክ የሚኖሩትን ሰዎች ከፈተና እንደሚያድናቸው፥ ኃጢአተኞችንም እንዴት እንደሚቀጣና ለፍርድ ቀንም እንዴት ጠብቆ እንደሚያቈያቸው ያውቃል ማለት ነው።