ኢሳይያስ 57:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ክፉ ሰዎች ግን እንደሚናወጥ ባሕር ናቸው፤ ውሃውም ቈሻሻውንና ጭቃውን ቀስቅሶ ያወጣል እንጂ ጸጥ አይልም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክፉዎች ግን ማዕበሉ ጭቃና ጕድፍ እንደሚያወጣ፣ ጸጥ ማለት እንደማይችል፣ እንደሚናወጥ ባሕር ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ክፉዎች ግን እንደሚንቀሳቀስ ባሕር ናቸው፤ ጸጥ ሊል አይችልምና፥ ውኆቹም ጭቃና ጉድፍ ያወጣሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ኃጥኣን ግን እንዲህ ይገለበጣሉ፤ ዕረፍትንም አያገኙም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ክፉዎች ግን እንደሚንቀሳቀስ ባሕር ናቸው፥ ጸጥ ይል ዘንድ አይችልምና፥ ውኆቹም ጭቃና ጕድፍ ያወጣሉና። |
ለሚመለከታቸው ሰው ፊታቸው ይመሰክርባቸዋል፤ እንደ ሰዶም ሰዎች ሳይደብቁ ኃጢአታቸውን በግልጽ ይናገራሉ፤ በራሳቸው ላይ ጥፋትን ስላመጡ ወዮላቸው።
“የሐማትና የአርፋድ ከተማ ነዋሪዎች የደማስቆን የጥፋት ወሬ ስለ ሰሙ ግራ ተጋቡ፤ ወደ ላይና ወደ ታች እንደሚናወጥ ባሕር የእነርሱም ልብ ተሸበረ።
እነዚህ ሰዎች ያለ ኀፍረት በመዳራት በአንድነት ግብዣችሁ ላይ ሲገኙ እንቅፋት ይሆኑባችኋል፤ እነርሱ የሚያስቡት ስለ ራሳቸው ብቻ ነው፤ በነፋስ እንደሚገፋ፥ ዝናብ እንደሌለው ደመና ናቸው። በፍሬ ወራት እንኳ ፍሬ እንደማይገኝበት፥ ከስሩ እንደ ተነቀለና ሁለት ጊዜ እንደ ሞተ ዛፍ ናቸው።
የአሳፋሪ ድርጊታቸውን ዐረፋ የሚደፍቁ፥ እንደ ተቈጣ የባሕር ማዕበል ናቸው፤ ድቅድቅ ጨለማ ለዘለዓለም እንደሚጠብቃቸውና፥ እንደሚንከራተቱ ኮከቦች ናቸው።