ኢሳይያስ 56:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የባዕድ አገር ሕዝቦች እንደ አራዊት እየፈነጩ መጥተው ሕዝቡን ይውጡ ዘንድ እግዚአብሔር አዞአቸዋል፤ እርሱም እንዲህ ይላል፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተ የምድር አራዊት ሁሉ ኑ፤ እናንተ የዱር አራዊት ሁሉ ኑና በጥርሳቸሁ ቦጫጭቁ! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተ የምድረ በዳ አራዊት ሁሉ፥ እናንተም የዱር አራዊት ሁሉ፥ ትበሉ ዘንድ ቅረቡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተ የምድረ በዳ አራዊት ሁሉ ኑ፤ እናንተ የዱር አራዊት ሁሉ ብሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተ የምድረ በዳ አራዊት ሁሉ፥ እናንተም የዱር አራዊት ሁሉ፥ ትበሉ ዘንድ ቅረቡ። |
ከወደ ምሥራቅ እንደ ነጣቂ ጭልፊት ያለውን እጠራለሁ፤ እርሱም ዓላማዬን የሚፈጽም፥ ከሩቅ አገር የሚመጣ ሰው ነው፤ የተናገርኩትን አደርጋለሁ፤ ያቀድኩትንም እፈጽማለሁ።
የመረጥኳቸው ሕዝቤ በሁሉ አቅጣጫ በጭልፊቶች እንደ ተከበበች ወፍ ሆነዋል፤ ስለዚህ ሌሎችም የዱር አራዊት መጥተው ሥጋቸውን በመብላት እንዲደሰቱ ጥሩአቸው።
አንተንና የወንዞችህን ዓሣዎች ሁሉ ወደ በረሓ እወረውራችኋለሁ፤ ሬሳህም ተነሥቶ ሳይቀበር በመሬት ላይ ወድቆ ይቀራል፤ ለወፎችና ለአራዊትም ምግብ እንዲሆን አደርገዋለሁ።
ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ “አንተም የሰው ልጅ ሆይ! ለተለያዩ የአሞራ ዘሮችና ለአራዊት ሁሉ እንዲህ በላቸው፦ ‘በእስራኤል ተራራዎች ላይ በማዘጋጅላችሁ ታላቅ የመሥዋዕት በዓል ሥጋን ለመብላትና ደምን ለመጠጣት ከየአቅጣጫው ተሰብስባችሁ ኑ።’