ዘፍጥረት 9:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሴምና ያፌትም ልብስ በስተኋላቸው፥ በትከሻቸው ያዙ፤ ወደ ድንኳኑም የኋሊት ሄዱና የአባታቸውን ራቊትነት እንዳያዩ ፊታቸውን አዙረው ራቊትነቱን ሸፈኑ፤ የአባታቸውንም ራቊትነት ኣላዩም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሴምና ያፌት ግን ልብስ ወስደው በጫንቃቸው ላይ አደረጉና የአባታቸውን ዕርቃነ ሥጋ እንዳያዩ ፊታቸውን አዙረው የኋሊት በመሄድ የአባታቸውን ዕርቃነ ሥጋ ሸፈኑ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሴምና ያፌትም ልብስ በትከሻቸው ላይ አደረጉ፥ የኋሊትም ሄደው የአባታቸውን ዕራቁትነት አለበሱ፤ ፊታቸውም ወደ ኋላ ነበረ፥ የአባታቸውንም ዕራቁትነት አላዩም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሴምና ያፌትም ልብስ ወስደው በጫንቃቸው ላይ አደረጉ፤ የኋሊትም ሄደው የአባታቸውን ዕራቁትነት አለበሱ፤ ፊታቸውም ወደ ኋላ ነበር፤ የአባታቸውንም ዕራቁትነት አላዩም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሴምና ያፌትም ሸማወስደው በጫንቃአው ላይ አደረጉ፥ የኋሊትም ሄደው የአባታቸወን ዕራቁትነት አለበሱ፥ ፊታቸውም ወደ ኋላ ነበረ፥ የአባታቸውንም ዕራቁትነት አላዩም። |
እንግዲህ ለበላይ ባለሥልጣን ሊደረግ የሚገባውን ሁሉ አድርጉ፤ ግብር ለሚገባው ግብርን፥ ቀረጥ ለሚገባው ቀረጥን ክፈሉ፤ መፈራት ለሚገባው መፈራትን፥ ክብር ለሚገባው ክብርን ስጡ።
ወንድሞች ሆይ! ሰው ተሳስቶ አንዳች ጥፋት አድርጎ ቢገኝ መንፈሳውያን የሆናችሁት እናንተ እንዲህ ዐይነቱን ሰው በገርነት አቅኑት፤ ነገር ግን አንተም በዚህ ዐይነት ፈተና እንዳትወድቅ ተጠንቀቅ።