La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 8:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ምድር እስካለች ድረስ፥ ለመዝራትና ለማጨድ፥ ለብርድና ለሙቀት፥ ለበጋና ለክረምት፥ ለቀንና ለሌሊት የማያቋርጥ ጊዜ ይኖራል።”

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“ምድር እስካለች ድረስ፣ የዘር ወቅትና መከር፣ ሙቀትና ቅዝቃዜ በጋና ክረምት፣ ቀንና ሌሊት፣ አይቋረጡም።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በምድር ዘመን ሁሉ መዝራትና ማጨድ፥ ብርድና ሙቀት፥ በጋና ክረምት፥ ቀንና ሌሊት አያቋርጡም።”

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በም​ድር ዘመን ሁሉ መዝ​ራ​ትና ማጨድ፥ ብር​ድና ሙቀት፥ በጋና ክረ​ምት፥ ቀንና ሌሊት አያ​ቋ​ር​ጡም።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በምድር ዘመን ሁሉ መዝራትና ማጨድ፥ ብርድና ሙቀት፥ በጋና ክረምት፥ ቀንና ሌሊት አያቋርጡም።

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 8:22
9 Referencias Cruzadas  

በምድር ላይ ራብ ከገባ ሁለተኛ ዓመቱን ይዞአል፤ ሰዎች አርሰው መከር መሰብሰብ የማይችሉባቸው አምስት ዓመቶች ገና ይመጣሉ።


“ሥራችሁን ሁሉ የምታከናውኑባቸው ስድስት ቀኖች አሉላችሁ፤ በእርሻም ሆነ በመከር ወራት በሰባተኛው ቀን ምንም ሥራ አትሥሩ።


ፀሐይን በቀን እንዲያበራ የሚያደርገው፥ ጨረቃና ከዋክብት በሌሊት እንዲያበሩ ሥርዓትን የወሰነላቸው፥ ባሕሩን በማዕበል እንዲናወጥ የሚቀሰቅሰው እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ስሙም የሠራዊት አምላክ ነው።


የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብ በወቅቱ የምሰጣችሁ፥ የመከርንም ወራት በየዓመቱ የማመላልስላችሁ እኔ ነኝ፤ እናንተ ግን እኔን ማክበርን ተዋችሁ።


ወንድሞች ሆይ! እንግዲህ ጌታ እስኪመጣ ድረስ በትዕግሥት ጠብቁ፤ ገበሬ መሬቱ የመጀመሪያውንና የኋለኛውን ዝናብ እስከሚያገኝ እየታገሠ ክቡር ዋጋ ያለውን የመሬቱን ፍሬ ይጠባበቃል።