ዘፍጥረት 6:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም ለአንተና ለእነዚህ ፍጥረቶች ሁሉ የሚበቃ ልዩ ልዩ ዐይነት ምግብ በመርከቡ ውስጥ አከማች።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለአንተና ለእነርሱ የሚያስፈልገውን ምግብ ሁሉ አከማች።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲሁም ለአንተና ለእነዚህ ፍጥረቶች ሁሉ የሚበቃ ልዩ ልዩ ዓይነት ምግብ በመርከቡ ውስጥ አከማች።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሚበላውም የመብል ዓይነት ሁሉ ለአንተ ውሰድ፤ ወደ አንተ ትሰበስባለህ፤ እርሱም ለአንተ፥ ለእነርሱም መብል ይሆናል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሚበላውም መብል ሁሉ ለአንተ ውሰድ፤ ወደ አንተም ትሰበስባለህ እርሱም ለአንተም ለእነርሱም መብል ይሆናል። |
እስቲ በሰማይ ላይ ወደሚበሩት ወፎች ተመልከቱ፤ እነርሱ አይዘሩም፤ አያጭዱም፤ በጐተራ አይከቱም፤ ነገር ግን የሰማዩ አባታችሁ ይመግባቸዋል። ታዲያ እናንተ ከወፎች እጅግ ትበልጡ የለምን?