ስለዚህ ሰውየው ወደ ይሁዳ ተመልሶ ሄደና “ላገኛት አልቻልኩም፤ በዚያ የሚኖሩትም ሰዎች ‘እንደዚህ ያለች አመንዝራ ሴት እዚህ የለችም’ አሉኝ” ብሎ ነገረው።
ዘፍጥረት 38:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይሁዳም “እንግዲህ ጠቦቱን ልኬላት ነበር፤ ነገር ግን ልታገኛት አልቻልክም፤ ስለዚህ ሰዎች መሳቂያ እንዳያደርጉን የወሰደችውን መያዣ እዚያው ታስቀረው” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይሁዳም፣ “እንግዲህ መያዣውን እንደ ያዘች ትቅር፣ አለዚያ መሣቂያ እንሆናለን። ለነገሩማ ይህን ፍየል ላክሁ፤ አንተም ፈልገህ አላገኘሃትም” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይሁዳም፥ “እንግዲህ መያዣውን እንደ ያዘች ትቅር፤ አለዚያ መሣቂያ እንሆናለን። ለነገሩማ ይህን ፍየል ላክሁ፤ አንተም ፈልገህ አላገኘሃትም” አለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይሁዳም፥ “እኛ መዘበቻ እንዳንሆን ትውሰደው፤ እነሆ፥ የፍየሉን ጠቦት ላክሁላት፤ አንተም አላገኘሃትም” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይሁዳም፦ እኛ መዘበቻ እንዳንሆን ትውሰደው እነሆ የፍየሉን ጠቦት ሰደድሁላት አንተም አላገኘሃትም አለ። |
ስለዚህ ሰውየው ወደ ይሁዳ ተመልሶ ሄደና “ላገኛት አልቻልኩም፤ በዚያ የሚኖሩትም ሰዎች ‘እንደዚህ ያለች አመንዝራ ሴት እዚህ የለችም’ አሉኝ” ብሎ ነገረው።
በሦስተኛው ወር ገደማ ሰዎች “ምራትህ ትዕማር የዝሙት ሥራ ፈጸመች፤ ከዚህም የተነሣ ፀንሳለች” ብለው ለይሁዳ ነገሩት። ይሁዳም “ወደ ውጪ አውጥታችሁ በእሳት አቃጥላችሁ ግደሉአት” አለ።
ታዲያ ትእዛዜን የናቅኸው ስለምንድን ነው? ይህንንስ ክፉ ነገር ለምን አደረግህ? ኦርዮን በጦር ሜዳ አስገደልከው፤ ንጹሑን ሰው ዐሞናውያን እንዲገድሉት አደረግህ፤ ሚስቱንም ወሰድክ!
ስውርና አሳፋሪ የሆነውን ነገር አስወግደናል፤ በተንኰልም አንሠራም፤ የእግዚአብሔርንም ቃል አንለውጥም፤ ይልቅስ እውነትን በይፋ እናሳያለን፤ ራሳችንንም ለሰው ሁሉ ኅሊና በእግዚአብሔር ፊት ግልጥ እናደርጋለን።
“እነሆ! እኔ እንደ ሌባ በድንገት እመጣለሁ! ራቁቱን እንዳይሆንና ኀፍረቱን ሰዎች እንዳያዩበት ነቅቶ ልብሱን የሚጠብቅ ሰው የተመሰገነ ነው!”