ወደ እኔ ወደ አገልጋያችሁ በመምጣታችሁ ደስ ብሎኛል፤ ስለዚህ ለጒዞአችሁ ብርታት የሚሰጣችሁን ጥቂት ምግብ አምጥቼ እንዳስተናግዳችሁ ፍቀዱልኝ።” እነርሱም “መልካም ነው፤ እንዳልከው አድርግ” አሉት።
ዘፍጥረት 18:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አብርሃም ወደ ድንኳኑ ሮጦ ሄደና ሣራን “ቶሎ ብለሽ ሦስት መስፈሪያ ዱቄት ውሰጂና አቡክተሽ እንጀራ ጋግሪ” አላት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አብርሃም በፍጥነት ሣራ ወዳለችበት ወደ ድንኳኑ ገብቶ፣ “ቶሎ ብለሽ ሦስት መስፈሪያ ስልቅ ዱቄት አቡኪና ቂጣ ጋግሪ” አላት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አብርሃምም ወደ ድንኳን ወደ ሣራ ዘንድ ፈጥኖ ገባና፦ “ሦስት መስፈሪያ የተሰለቀ ዱቄት ፈጥነሽ አዘጋጂ፥ ለውሺውም፥ እንጎቻም አድርጊ” አላት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አብርሃምም ወደ ድንኳን ወደ ሚስቱ ወደ ሣራ ፈጥኖ ገባና፥ “ሦስት መስፈሪያ የተሰለቀ ዱቄት ፈጥነሽ ለውሺ፤ እንጎቻም አድርጊ” አላት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አብርሃምም ወደ ድንኳን ወደ ሣራ ዘንድ ፈጥኖ ገባና፥ ሦስት መስፈሪያ የተሰለቀ ዱቄር ፈጥነሽ አዘጋጂ፥ ለውሺውም እንጎቻም አድርጊ አላት። |
ወደ እኔ ወደ አገልጋያችሁ በመምጣታችሁ ደስ ብሎኛል፤ ስለዚህ ለጒዞአችሁ ብርታት የሚሰጣችሁን ጥቂት ምግብ አምጥቼ እንዳስተናግዳችሁ ፍቀዱልኝ።” እነርሱም “መልካም ነው፤ እንዳልከው አድርግ” አሉት።
ከዚህ በኋላ አብርሃም ወደ መንጋው ሄደና ለግላጋውንና መልካሙን ጥጃ መርጦ ለአገልጋዩ ሰጠው፤ አገልጋዩም በፍጥነት ዐርዶ አወራርዶ አዘጋጀው፤
ነገር ግን ወደ ቤቱ እንዲገቡ አጥብቆ ስለ ለመናቸው፥ ከእርሱ ጋር ወደ ቤቱ ገቡ፤ ከዚህም በኋላ ሎጥ እንጀራ ጋግረው መልካም ራት እንዲያዘጋጁ ለአገልጋዮቹ ነገራቸው፤ ራትም በተዘጋጀ ጊዜ እንግዶቹ በሉ።
ስለዚህም አምኖን የታመመ በመምሰል በአልጋው ላይ ተኛ። ንጉሥ ዳዊትም ሊጠይቀው ወደ እርሱ በሄደ ጊዜ አምኖን “እኅቴ ትዕማር እዚህ በአጠገቤ እያየኋት ሁለት እንጀራ ጋግራ እርስዋ ራስዋ እንድታቀርብልኝ ፍቀድላት” አለው።
ደግሞም ኢየሱስ ይህን ምሳሌ ነገራቸው፦ “መንግሥተ ሰማይ አንዲት ሴት ወስዳ ከሦስት መስፈሪያ ዱቄት ጋር የለወሰችውን እርሾ ትመስላለች፤ እርሾውም ሊጡን ሁሉ እንዲቦካ አደረገው።”
እርስዋና በቤትዋ ያሉ ሰዎች ሁሉ ከተጠመቁ በኋላ፥ “በጌታ የማምን መሆኔን ካረጋገጣችሁልኝ ወደ ቤቴ መጥታችሁ ተቀመጡ” ስትል አጥብቃ ለመነችን።
ወንድሞቼ ሆይ! እናንተ ለነጻነት ተጠርታችኋል፤ ነገር ግን አንዱ ሌላውን በፍቅር ያገልግል እንጂ ይህ ነጻነታችሁ የሥጋን ምኞት መፈጸሚያ ምክንያት አይሁን።
እንግዳ ተቀብሎ ማስተናገድን አትርሱ፤ እንደዚህ እንግዶችን እየተቀበሉ በማስተናገድ አንዳንድ ሰዎች ሳያውቁ መላእክትን ተቀብለው አስተናግደዋል።
ጌዴዎንም ወደ ቤት ገባና የፍየል ጠቦት ዐርዶ አዘጋጀ፤ ዐሥር ኪሎ የሚያኽልም ዱቄት ወስዶ እርሾ ያልገባበት እንጀራ ጋገረ፤ ሥጋውን በመሶብ፥ መረቁን በምንቸት አድርጎ በወርካው ሥር ለተቀመጠው ለእግዚአብሔር መልአክ ወስዶ አቀረበለት።