ዘፀአት 26:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ዐይነት በእያንዳንዱ ተራዳ ሥር ሁለት እግር ሆኖ ዐሥራ ስድስት የብር እግሮች ያሉአቸው ስምንት ተራዳዎች ይኖራሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ስምንት ወጋግራዎች አሉ፤ እንዲሁም ዐሥራ ስድስት የብር መቆሚያዎች ሲኖሩ፣ ለእያንዳንዱ ወጋግራ ሁለት ሁለት መቆሚያ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስምንት ሳንቃዎችና ዐሥራ ስድስት የብር እግሮቻቸው ይሁኑ፥ ከእያንዳንዱም ሳንቃ በታች ሁለት እግሮች ይሆናሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስምንት ሳንቆችና ዐሥራ ስድስት የብር እግሮቻቸው ይሁኑ፤ ከእያንዳንዱም ሳንቃ በታች በሁለቱም መጋጠሚያዎች ሁለት ሁለት እግሮች ይሆናሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስምንት ሳንቆችና አሥራ ስድስት የብር እግሮቻቸው ይሁኑ፤ ከእያንዳንዱም ሳንቃ በታች ሁለት እግሮች ይሆናሉ። |
እነዚህ በማእዘኖቹ ላይ ያሉት ተራዳዎች ከታች በኩል ተጣምረው እስከ ላይ አንደኛው ዋልታ መያያዝ አለባቸው፤ ሁለቱን ማእዘኖች የሚያገናኙት ሁለት ተራዳዎች በዚሁ ዐይነት ይሠሩ።
ከብሩም ሦስት ሺህ አራት መቶ ኪሎ የሚሆነው ለተቀደሰው ድንኳንና ለመጋረጃዎች መቆሚያ የሚሆኑ አንድ መቶ እግሮች የተሠሩበት ነበር፤ ይኸውም ለእያንዳንዱ እግር ሠላሳ አራት ኪሎ ግራም ተመድቦለት ነው።