ዘዳግም 32:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ተከታታይ ጥፋት አመጣባቸዋለሁ፤ ፍላጻዎቼን ሁሉ በእነርሱ ላይ እጨርሳለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በመዓት ላይ መዓት አመጣባቸዋለሁ። ፍላጻዬንም በእነርሱ ላይ እጨርሳለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “‘በመዓት ላይ መዓት አመጣባቸዋለሁ፤ ፍላጻዬንም በእነርሱ ላይ እጨርሳለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለመከራ እሰበስባቸዋለሁ፤ ፍላጻዎችንም እጨርስባቸዋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መከራን እጨምርባቸዋለሁ፤ 2 በፍላጾቼም እወጋቸዋለሁ። |
አምላክ ሆይ! የምድራችንን ወሰን በየአቅጣጫው በማስፋት መንግሥታችንን ከፍ ከፍ አደረግህ፤ ሕዝባችንንም አበዛህ፤ ይህም አንተ የምትከብርበት ሆኖአል።
ልዑል እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፦ “ሕዝብንና እንስሶችን በአንድነት ለመጨረስ ጦርነትን፥ ራብን፥ አራዊትንና ቸነፈርን እነዚህን እጅግ የከፉ አራት መቅሠፍቶች በኢየሩሳሌም ላይ አመጣለሁ።
እንደ ገዳይ ቀስት የሆነውን ራብ የማመጣባችሁ እንዲያጠፋችሁ ነው፤ ደጋግሜ ራብን አመጣባችኋለሁ፤ የምግብ አቅርቦታችሁም እንዲቋረጥ አደርጋለሁ።
ሽማግሌ ሆነ ወጣት ወንዶችና ሴቶች፥ ሕፃናትንና ሴቶችን ሁሉ ግደሉ፤ ነገር ግን በግንባሩ ላይ ምልክት ያለበትን ማንንም አትንኩ፤ ግድያውንም ከዚሁ ከቤተ መቅደሴ ጀምሩ፤” ስለዚህ እዚያ በቤተ መቅደስ ከቆሙት መሪዎች አንሥተው ግድያውን ማካሄድ ጀመሩ።
“ነገር ግን ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ባትታዘዝና እኔ ዛሬ የምሰጥህንም ሕጎችና ትእዛዞች በታማኝነት ባትጠብቅ ከዚህ የሚከተለው መርገም ሁሉ ይደርስብሃል፦
እግዚአብሔር እንደዚህ ያለውን ሰው በዚህ የሕግ መጽሐፍ በተጻፈው የእርግማን ቃል ኪዳን መሠረት ከእስራኤል ነገዶች መካከል አውጥቶ ያጠፋዋል።