ዘዳግም 27:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዮርዳኖስን በተሻገርህ ጊዜ እኔ ዛሬ ባዘዝኩህ መሠረት እነዚህን ድንጋዮች በዔባል ተራራ ላይ አቁመህ በኖራ ለስናቸው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዮርዳኖስን እንደ ተሻገርህም፣ ዛሬ ባዘዝሁህ መሠረት እነዚህን ድንጋዮች በጌባል ተራራ ላይ ትከላቸው፤ በኖራም ቅባቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዮርዳኖስን እንደ ተሻገርህም፥ ዛሬ ባዘዝሁህ መሠረት እነዚህን ድንጋዮች በጌባል ተራራ ላይ ትከላቸው፤ በኖራም ምረጋቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮርዳኖስንም በተሻገራችሁ ጊዜ፥ ዛሬ እንዳዘዝኋችሁ፥ እነዚህን ድንጋዮች በጌባል ተራራ አቁሙ፤ በኖራም ምረጓቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዮርዳኖስንም በተሻገርህ ጊዜ፥ ዛሬ እንዳዘዝሁህ፥ እነዚህን ድንጋዮች በጌባል ተራራ አቁም፥ በኖራም ምረጋቸው። |
የዮርዳኖስን ወንዝ ተሻግራችሁ አምላክህ እግዚአብሔር ወደሚሰጥህ ምድር በምትገባበት ጊዜ ታላላቅ የሆኑ ጥቂት ድንጋዮችን አቁመህ በኖራ ለስነው፤