አሁን ግን እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የአንድ ጊዜያዊ የቅጥር ሠራተኛ የሥራ ጊዜ እንደሚቋረጥ የሞአብ ክብርና ብዙ ሕዝቦችዋ በሦስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ይዋረዳል፤ ከሕዝቧ የተረፉትም በጣም ጥቂቶችና ደካሞች ይሆናሉ።”
ዘዳግም 15:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱንም ነጻ ባወጣኸው ጊዜ አንድ ተቀጣሪ ለስድስት ዓመት ከሚሰጥህ እጥፍ አገልግሎት ስለ ሰጠህ ቅር አይበልህ። እንግዲህ ይህን አድርግ፤ እግዚአብሔርም በምትሠራው ሁሉ ይባርክሃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አገልጋይህን ዐርነት ማውጣቱ ከባድ መስሎ አይታይህ፤ የስድስት ዓመት አገልግሎቱ፣ አንድ የቅጥር ሠራተኛ የሚሰጠው አገልግሎት ዕጥፍ ነውና። አምላክህ እግዚአብሔር በምታደርገው ነገር ሁሉ ይባርክሃል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአገልጋይህን የስድስት ዓመት አገልግሎቱ፥ አንድ የቅጥር ሠራተኛ ከሚሰጠው አገልግሎት ዕጥፍ ነውና፤ እርሱን ነጻ ማውጣቱ ከባድ መስሎ አይታይህ። ጌታ እግዚአብሔር በምታደርገው ነገር ሁሉ ይባርክሃል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱንም አርነት ባወጣኸው ጊዜ የምንደኝነቱን ሥራ ሁለት ዕጥፍ አድርጎ ስድስት ዓመት አገልግሎሃልና አያስጨንቅህ፤ አምላክህም እግዚአብሔር በምትሠራው ሁሉ ይባርክሃል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱንም አርነት ባወጣኸው ጊዜ የምንደኝነቱን ሥራ ሁለት እጥፍ አድርጎ ስድስት ዓመት አገልግሎሃልና አይክበድህ፤ አምልካህም እግዚአብሔር በምትሠራው ሁሉ ይባርክሃል። |
አሁን ግን እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የአንድ ጊዜያዊ የቅጥር ሠራተኛ የሥራ ጊዜ እንደሚቋረጥ የሞአብ ክብርና ብዙ ሕዝቦችዋ በሦስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ይዋረዳል፤ ከሕዝቧ የተረፉትም በጣም ጥቂቶችና ደካሞች ይሆናሉ።”
ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፤ “የሠራተኞች የሥራ ውል እንደሚያልቅ ልክ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ የቄዳር ነገዶች ክብር ይወገዳል፤
ይህም ከሆነ ወደ ቤትህ ደጃፍ ወስደህ ጆሮውን በወስፌ ብሳው፤ ከዚያም በኋላ እስከ ዕድሜው ፍጻሜ ድረስ የአንተ ባሪያ ይሆናል፤ ለሴት ባሪያህም ቢሆን ይህንኑ አድርግ።
“ከከብትህ ወይም ከበግህ መንጋ የሚወለደውን ወንድ የሆነ በኲር ሁሉ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር የተለየ እንዲሆን አድርግ፤ በኲር የሆኑትን በሬዎች ለማንኛውም ተግባር አትጠቀምባቸው፤ እንዲሁም ከበጎች መንጋ በኲሮችን ጠጒራቸውን አትሸልት፤